1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዚዳንት ባይደን የአዉሮጳ ጉብኝት 

ዓርብ፣ ሰኔ 4 2013

ፕሬዚዳንት ባይደን ዛሬ በጀመረዉ የቡድን ሰባት ጉባኤ ከተካፈሉ በኋላ የፊታችን ሰኞ የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነዉ በብራስልስ በሚገኘዉ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገሮች ማለትም በ «ኔቶ» የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚካፈሉ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/3ulsX
G7-Gipfel in St Ives 2021 | Gruppenfoto
ምስል Patrick Semansky/AP/picture alliance

የባይደን የመጀመርያ የአዉሮጳ ጉብኝት

 

የዩናትድ ስቴትስን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከያዙ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አዉሮጳ የመጡት ጆባ ይደን ኮርንዋል በተባለዉ የብሪታንያ የባህር ዳርቻ በሚካሄደዉ ቡድን 7 በመባል የሚታወቁት ባለጸጋዎቹ ሃገራት ጉባዔ ለመካፈል እንጊሊዝ ከገቡ ሁለተኛ ቀናቸዉን ይዘዋል። ፕሬዚዳንት ባይደን ዛሬ በጀመረዉ የቡድን ሰባት ጉባኤ ከተካፈሉ በኋላ የፊታችን ሰኞ የአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነዉ በብራስልሱ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ሃገሮች ማለትም በ «ኔቶ» የመሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚካፈሉ ይጠበቃል። የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የአዉሮጳ ጉብኝት እና አንደምታዉን በተመለከተ፤ የብረስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ