1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰባሰብ መጀመር

ረቡዕ፣ የካቲት 20 2011

ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አንድ የሚያመጣቸውን የቅድመ ግንባር ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አድርገዋል። ፓርቲዎቹ ግንባር ለመፍጠር የተስማሙት ስድስት ወራት ከወሰደ ውይይት በኋላ ሲሆን የግንባሩ ምስረታም በሁለት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/3ECxK
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

የሰባት ፓርቲዎች ስምምነት

 

 ስምምነቱን የተፈራረሙት፤ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት ኢዲዩ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ መኢብአፓ፣ የአፋር ህዝቦች ፍትኃዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የአፋር ህብረት ነጻነት ፓርቲ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝቦች ፍትኃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች ናቸው። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በምሕፃሩ መኢአድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ ይህ ምን ማለት እንደሆነ እንዲያብራሩ ተስፋለም ወልደየስ ጠይቋቸዋል።

ተስፋለም ወልደየስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ