1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ሂደት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 2 2012

የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በበፊቱ ሕግ ላይ ያለውን መስፈርት ያሟሉ በመኾናቸው እና አዲሱ ሕግ ከመውጣቱ በፊት፤ ከነሐሴ በፊት የሚገባውን ነገር ኹሉ ሰነድ አሟልተው ጨርሰው አስገብተው ያጠናቀቁ ስለነበሩ ነው።

https://p.dw.com/p/3Ui9x
Äthiopien Wahlkommission
ምስል NEBE

የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በቀድሞ ሕግ ላይ ያለውን መስፈርት ያሟሉ ናቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ የነበሩ ላላቸዉ ዘጠኝ ተጨማሪ ፓርቲዎች እዉቅና መስጠቱን አስታወቀ። ምርጫ ቦርድ «የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ» የምስክር ወረቀት ለፓርቲዎቹ የተሰጠው በአዲሱ ሕግ ሳይሆን በቀድሞዉ «537 በሚባለው ሕግ» መሰረት ለተመዘገቡ መሆኑን ገልፃል። የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳይ አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ይህንኑ ለዶይቸ ቬለ ዛሬ በሰጡት ቃለ ምልልስ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በቀድሞ ሕግ ላይ ያለውን መስፈርት ያሟሉ በመሆናቸው እና አዲሱ ሕግ ከመውጣቱ በፊት፤ ከነሐሴ በፊት የሚገባውን ነገር ኹሉ ሰነድ አሟልተው ጨርሰው አስገብተው ያጠናቀቁ ስለነበሩ መሆኑን ተናግረዋል።

እውቅና የተሰጣቸው ዘጠኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አፋር ህዝባዊ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህፍዴፓ)፣ አፋር ህዝብ ነጻነት ፓርቲ (አህነፓ)፣ ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ)፣ ቁጫ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)፣ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)፣ ዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እንዲሁም ሱማሌ አንድነት ፓርቲ (ሱአፓ) ናቸው። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚሕ ቀደም ለ71 የፖለቲካ ፓርቲዎች እዉቅና ሰጥቶ ነበር።  ስለ ፖለቲካ ፓርቲዉ የምዝገባ ሂደት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስን አነጋግረናል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ