1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር

ዓርብ፣ የካቲት 26 2002

የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳ ከተጀመረ ወዲህ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራዲዮ ድርጅት አዘጋጅነት ክርክር አካሂደዋል።

https://p.dw.com/p/MLRw
ምስል picture alliance/dpa

እስካሁን ፓርቲዎቹ የተከራከሩባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች ዴሞክራሲና የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት እንዲሁም ፌደራሊዝም ያልተማከለ አስተዳደር በኢትዮጵያ የተሰኙት ናቸዉ። በሌላ በኩል በድሬደዋ ለምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች ዓላማቸዉን ለህዝብ የሚያስተዋዉቁበት የራዲዮና የቴሌቪዥን የአየር ጊዜ ድልድል ላይ አልተካተትንም ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ። የብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ በበኩሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድልድሉ ተካተዋል፤ የግሎቹ ግን ቦታ አልተያዘላቸዉም ይላል።

ዘገባዎቹን በተከታታይ በመጫን ያዳምጡ!

ታደሰ እንግዳዉ፤ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ