የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉይይት

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:02 ደቂቃ
11.01.2019

ነፃና ገለልተኛ አደራዳሪ

በኢትዮጵያ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገዉን ዉይይቶች የሚያቃና 16 አንቀፆች ያሉት ስርዓትና ደንብ መፅደቁን ተሳታፊዎች ለDW ተናግረዋል። ነፃና ገለልተኛ ሆነው ዉይይቱን የሚመሩ ሰዎች ስም ዝርዝር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲያቀርቡ መጠየቃቸዉንም ገልፀዋል። ለዉይይቱም ፖለቲካ ፓርቲዎቹ 32 አጄንዳዎች መርጠዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አዘጋጅነት በአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ለመትከል እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገናኝተው የሚወያዩበትን መድረክ የሚያመቻችበትን ሀሳብ መሰረት ያደረገ ነዉ የተባለ የሁለት ቀን አዉደ-ጥናት ትናንት ተጠናቀዋል።

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ ይህ አዉደ-ጥናት 16 አንቀፆች ያሉት ስርዓትና ደንብ መፅደቁን ለመረዳት ተችለዋል። የፀደቀው የስርዓትና ደንቡ ዋና አላማም የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት በሚያደርጉበት ወቅት የሚመሩባቸውን መርሆዎች፣ ውይይቱ የሚካሄድበት ስርዓት፣ ከውይይቱ ተሳታፊዎች የሚጠበቅ ኃላፊነት፣ የአወያዮች ኃላፊነትና ግዴታ፣ የመገናኛ ብዙኃን ሚና እና ሌሎች አንቀፆች ማካተቱን በአዉደ-ጥናቱ ላይ የተገኙት ለDW ተናግረዋል።

ነፃና ገለልተኛ ሆኖ ዉይይቱን የሚመሩ ሰዎች ስም ዝርዝር በፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲቀርብም ምርጫ ቦርድ መጠየቁንም DW ያነጋገራቸዉ ተሳታፍዎች ገልፀዋል። ቀደም ሲል በነበሩት ዉይይቶች ላይ ገለልተኛ አካል ካልቀረበ በሚል በመድረኮቹ ላይ ያልተሳተፉት ፖለቲካ ፓርቲዎች አዲሱ ደንብ እንዳስደሰታቸዉ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግሬስ /ኦፌኮ/ በዉይይቶቹ ላይ ካልተሳተፉት ዉስጥ አንዱ ናቸዉ። የኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር አቶ ሙላቱ ገማቹ የአሁኑ ከበፊቱ የተለየ እንደሆነ ገልጸዋል።

ካሁን ቀደም በተካሄዱት ዉይይቶች ላይ ገለልተኛ አደራዳሪ ይቅረብ በሚል ምክንያት ካልተሳተፉት ዉስጥ የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ይገኝበታል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ እንዲወያዩባቸው በተመረጡት 32 አጄንዳዎች ውስጥ የምርጫ ቦርድ፣ የቀጣዩ ምርጫ፣ የሕገ-መንግስትና ፌዴራልዝም፣ እንዲሁም፣ የፖለቲካ ፓርትዎች ጉዳዮች ዋናዎቹ መሆናቸዉን የአዉደ-ጥናቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

አጄንዳዎቹ የሁሉም ተሳታፊዎች ናቸዉ ማለት ይቻላል የሚሉት አቶ የሽዋስ አጄንዳዎችን ዉጤታማ ለማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

አጄንዳዎቹ ጊዝያዊነትን የጠበቁ እና የህብረተሰቡን ፍላጎት የሚያጎሉ መሆን እንዳለባቸው የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ አሳስበዋል።

በየ 15 ቀኑ በተከታታይ ይካሄዳል የሚባለው ዉይይት በቅርብ እንደሚጀመር አቶ የሽዋስ አስታውቀዋል። 

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

ተከታተሉን