1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖላንዱ ረቂቅ ሕግና ተቃውሞው

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 25 2008

የፖላንድ መንግሥት እጅግ አወዛጋቢ የተባለውን አዲሱን የመገናኛ አውታሮች ሕግ ባለፈው ሣምንት በምክር ቤት ማፅደቁ በአውሮጳ ሕብረት በኩል ተቃውሞ አስነስቷል። ሕጉ በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ተፈርሞ ተግባራዊ ከሆነ የመገናኛ አውታሮችን ነፃነት ይገድባል የሚል ፍራቻ አስነስቷል። የፖላንድ መንግሥት አዲሱን ሕግ በተመለከተ

https://p.dw.com/p/1HXoh
Rücktrittswelle im öffentlich-rechtlichen Fernsehen Polens
ምስል picture-alliance/dpa/L. Szymanski

[No title]

ትናንት ከአውሮጳ ሕብረት በኩል የተሰነዘረበት ነቀፌታ እንዳስገረመው ገልጧል። አዲሱ ሕግ ቀደም ሲል የተሾሙ በመንግሥት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሬዲዮኖች እና ቴሌቪዥኖች ሥራ አስኪያጆችን የሥራ ዘመን እንዲያበቃ ያስችላል። ከዚያ በተጨማሪ ሕጉ መንግሥት አዲስ ሥራ አስኪያጆችን መሾም እንዲችል ያደርጋል ተብሎለታል። የፖላንድን አዲሱን የመገናኛ አውታሮች ሕግ በተመለከተ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ቃለ-መጠይቅ አድርጌለት ነበር። ሕጉ ከአውሮጳ ሕብረት ለምን ተቃውሞ እንዳስነሳ በማብራራት ይጀምራል።

አዲሱ የፖላንድ የመገናኛ አውታሮች ሕግ በምክር ቤት ከጸደቀ በኋላ 4 የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች አስተዳዳሪዎች ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። አዲሱ ሕግ በፖላንድ ፕሬዚዳንት አንድሪዬ ዱዳ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ