1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖላንድ ዜጎች በብሪታንያ የገጠማቸው ችግር

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 1 2008

ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት ለመውጣት ባለፈው ሰኔ ወር በሬፈረንደም ከወሰነች ወዲህ በሀገሪቱ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ችግር ላይ ይገኛሉ። የውጭ ዜጎች የጥላቻ እና የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ ሆነዋል። ጥቃቱ በተለይ የፖላንድ ዜጎችን የነካ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት አንድ የፖላንድ ዜጋ በዘረኝነት ሰበብ በተጣለ ጥቃት ተገድሏል፣ ሌሎች ሶስትም ቆስለዋል።

https://p.dw.com/p/1JwfG
England Polnischer Mann von Jugendlichen getötet
ለተገደለው ፖላንዳዊ የሀዘን መግለጫምስል picture-alliance/AP Photo/D. McCrudden

[No title]

በብሪታንያ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ ካለፈው ሰኔ ወር በኋላ 16 ጊዜ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። የፖላንድ እና የብሪታንያ ባለስልጣናት አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው ስለዚሁ ጉዳይ በተደጋጋሚ ተወያይተዋል። አንድ የፖላንድ የልዑካን ቡድን አሁንም ለንደን፣ ብሪታንያ ይገኛል። የልዑካን ቡድን በብሪታንያ ያሉትን ዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚቻልበትን መፍትሔ የማፈላለግ ዓላማ ይዞ ነው ወደ ለንደን የተጓዘው።

ስለሺ ይልማ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ