1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ ሱ ጉትንበርግ አነሳስና አወዳደቅ

ማክሰኞ፣ የካቲት 29 2003

ከፌደራል ጀርመን መንግስት ካቢኔ አባላት የህዝብ ፍቅር የተትረፈረፈላቸው ዝነኛ ፖለቲከኛ ነበሩ ። የዛሬ 5 ለዶክትሪት ዲግሪ ካቀረቡት የመመረቂያ ፅሁፍ ሀያ በመቶው ያህል ከሌሌች ፅሁፎች በቀጥታ የተገለበጡ መሆናቸው ተደጋግሞ ከተወሳና ከተረጋገጠ በኋላ ከሃላፊነታቸው ቢሰናበቱም ፣ አሁንም ለምን ወረዱ የሚሉ ደጋፊዎቻቸው ጥቂት አይደሉም ።

https://p.dw.com/p/R7KW
ሱ ጉትንበርግምስል picture alliance/dpa

እስከ ዛሬ ሳምንት ድረስ የጀርመን መከላከያ ሚኒስትር የነበሩት የካርል ቴዎዶር ሱ ጉትንበርግ አነሳስና አወዳደቅ የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ካርል ቴዎዶር ሱ ጉትንበርግ ከጀርመን ሚኒስትሮች በወጣትነትና በሽቅርቅርነት ስማቸው ይነሳል ። መልከ መልካምና አይነ ግብ እንዲሁም ከሁሉም በላይ የጀርመን የቀድሞ የገዥ መደብ የዘር ሃረግ ያላቸው መሆኑ የብዙዎችን ትኩረት እንዲስቡና እንዲወደዱም ምክንያቶች መሆናቸው ይወሳል ። ከዚህ በመነሳትም ወደፊት ለመራሄ መንግስትነትን ሥልጣን ሊበቁ ይችላሉ ተብሎ ሲተነበይላቸውም ነበር ። ሆኖም የጥምሩ መንግስት አካል የሆነው የክርስቲያን ሶሻል ህብረት CSU ፓርቲው ሚኒስትር ሱ ጉትንበርግ በአንድ ጋዜጣ ሾልኮ በወጣ የተደበቀ ቅሌት ሰበብ ሳያስቡት ባለፈው ሳምንት ከያዙት ከፍተኛ ሃላፊነት እስከ መሰናበት ደርሰዋል ።

Flash-Galerie Zu Guttenberg Rücktritt
የ ሱ ጉትንበርግ ስንበትምስል dapd

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ