1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ «ዞን 9» የፍርድ ቤት ቀጠሮ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 20 2008

የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በ«ዞን 9» ጦማሪያን ላይ ያቀረበውን አቤቱታ እና የጠበቃውን መልስ አገናዝቦ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ይዞት የነበረውን ቀጠሮ ወደ ግንቦት 17 አራዝሞታል።

https://p.dw.com/p/1ILT1
Äthiopien Zone9 Blogger Gruppe
ምስል Zone9

[No title]

ብይኑ የተራዘመው ካሁን ቀደም በመቅረጫ ድምፅ የተያዘው ክርክር በፅሑፍ ተገልብጦ ለፍርድ ቤቱ እና ለዳኞቹ የቀረበው ከጥቂት ጊዜ በፊት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን አድምጦ ውሳኔ ለመስጠት በቂ ጊዜ ባለማግኘቱ ምክንያት መሆኑን ዳኞቹ ገልጸዋል። የዛሬውን የፍርድ ቤት ችሎት የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታትሏል። የ«ዞን 9» ጠበቃንም አነጋግሯል።

ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ