1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ 2019 የባህል መሰናዶ ቅኝት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 9 2012

ሊጠናቀቅ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት በቀረዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት የባህል መሰናዶ የተለያዩ ርዕሶችን ዳስዋል። በዓመቱ በባህል መድረክ ከቀረቡ ርዕሶች መካከል አበይት ያልናቸዉን ርዕሶች ጨምቀን መሰናዶ ይዘናል።

https://p.dw.com/p/3V6am
Äthiopien neuer politischer Führer ist auf Unterstützung der Jugend angewiesen
ምስል Reuters/T. Negeri

የ 2019 የባህል መሰናዶ ቅኝት

 

ሊጠናቀቅ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት በቀረዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 ዓመት የባህል መሰናዶ የተለያዩ ርዕሶችን ዳስዋል። ኢትዮጵያ የመጥፋት ስጋት የተደቀነባቸው ቋንቋዎች፤ በምዕራባዉያን የተዘረፉ ቅርሶችን ማስመለስ፤ የአፄ ቴዮድሮስ 200ኛ ዓመት አከባበር፤ መቶ ዓመት ያስቆጠረዉ የአማርኛ ትምህርት በሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ ፤ የቤተ- እስራኤላዉያኑ ከባዱ ምልሰት ጉዳይ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሲመትና የኪነጥበብ ሚና፤ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ ፤ 25ኛ ዓመት የዓለምከተማና የፋተርሽቴትን ወዳጅነት ምስረታ፤ የ7 ቤት አገው የፈረሰኞች ማህበር በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ መጠየቁ፤ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ ቤት በሃራሬ ዚምባቤ ፤ ሪታ ፓንክኸርስት የኢትዮጵያ ባለውለታ እንዲሁም ከቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍስሃ ደስታ ጋር የተደረገ ቆይታ ፤ በዓመቱ በባህል መድረክ ከቀረቡ ርዕሶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ። እነዚሁ ርዕሶችን ጨምቀን መሰናዶ ይዘናል።

Frankreich Paris | Zerstörung nach Brand der Kathedrale Notre-Dame de Paris
ምስል Reuters/C. Petit Tesson

«በመጥፋት ላይ ያሉ ቋንቋዎች» 

የሥነ ቋንቋ ዘርፍ ባለሙያዎች እንደሚሉት ቋንቋ የሰዎችን ባህል ፤ ወግ ፤ አኗኗርና ውስጣዊ ስሜታቸውን ለመግለጽ የሚያገልግል መሳሪያ ነው። በአጽናፋዊ ትስስር (ግሎባላይዜሽን)ዓለማችን ከ 7000 ሺህ በላይ ቋንቋዎች እንደሚነገሩ ይዘገባል። የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መኖርያ በሆነችዉ በኢትዮጵያም ከ 80 በላይ ቋንቋዎች እንደሚነገሩ መዛግብት ያሳያሉ። ይሁን እንጂ ለቋንቋዎች ጥበቃ ባለመሰራቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይበሉ ቋንቋዎች ጠፍተዋል እንዳንዶቹ ደግሞ በመጥፋት አደጋ ላይ እንደሚገኙ፤ የኢትዮጲያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በተለያዩ ጊዚያት ያካሄዳቸው ጥናቶች ያመለከታሉ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል 21 በመቶ ያህሉ የጉዳት ወይም የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው መሆናቸዉን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ልሳንና የሥነ-ተግባቢት መምህር የሆኑት ዶክተር ፈቀደ ምኖታ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

«የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት 100ኛ ዓመት በሀምቡርግ»    

Älteste äthiopische Bibelhandschrift
ምስል DW/ A.T.Hahn

በጎርጎሮሳዊዉ 1919 ዓ.ም የተመሠረተዉ እና ዘንድሮ 100ኛ ዓመቱን ያከበረዉ የሀምቡርግ ዩንቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሲሰጥበት ዘንድሮ መቶ ዓመት መድፈኑ ሌላዉ የባህል መድረክ የዘንድሮ ዋንኛ ርዕስ ነበር። አማርኛ ቋንቋ በጀርመን ዩንቨርሲቲዎች በ1919 ዓ.ም መሰጠት ይጀምር እንጅ ቀደም ሲልም ቢሆን ኢትዮጵያ ለጀርመኖች ትልቅ የምርምርና ጥናት ሀገር ሆና መቆየትዋን ዩንቨርስቲዉ የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ስር የአፍሪቃና የኢትዮጵያ ጥናት ትምህርት ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህርና የአፍሪቃ ሥነ-ቃል ተመራማሪ ዶክተር ጌቴ ገላዬ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የራሳቸዉ ጽሕፈት፣ ታሪክ ፣ነፃ የመንግሥት አወቃቀር፣ ጥንታዊ የስልጣኔ ካላቸዉና ነፃነታቸዉን ጠብቀዉ ከቆዩ ጥቂት ሃገራት መካከል አንዷ በመሆኗ ጀርመናዉያኑ ምሁራን  ከ17ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነበር በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ማድረግ የጀመሩት።

በጎርጎረሳዉያኑ 2019 ዓመት መጀመርያ ማለትም ጥር ወር 2011 ዓ.ም ኢትዮጵያዉያን የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን የ200ኛ ዓመት የልደት በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል። በተለይ በጎንደርና አካባቢዋ ብሎም በባህር ዳር የተለያዩ የሥነ-ጽሑፍና እና የመነባንብ መድረኮችን በማዘጋጀት አስበዋል። የጎንደር ባህል ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳረጋይ ደሌ በሰጡን አስተያየት ተናግረዋል።  

«ዝክረ ዓድዋ»

Äthiopien 199. Geburtstagsfeier Kaiser Tewodros II.
ምስል Gebeyehu Begashaw

አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው! ካሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለሚሽትህ፥ ለሃይማኖትህ፥ ለሀገርህ ስትል በሐዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጠላኛለህ ፣ አልተውህም! ማርያምን! ለዚህ አማላጅ የለኝም!  ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና እስከ ጥቅምት እኩሌታ የሸዋ ሰው ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ።» ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ

ታላቁ የጥቁር ህዝብ ድል ዓድዋ የጀመረው ከጦርነቱ በፊት ህዝቡ የንጉሠ ነገስቱን ጥሪ ሰምቶ ከጫፍ ጫፍ የተመመ ዕለት ነው። መነሻው ላይም ድል አድራጊነት መንፈስ ነበር።  አድዋ ጉዞ 6 በገፃቸዉ ላይ ያስቀመጡት ጽሑፍ ነዉ።

Äthiopien 199. Geburtstagsfeier Kaiser Tewodros II.
ምስል Gebeyehu Begashaw

የካቲት ታላላቅ ገድሎች የተፈጸሙበትና አንፀባራቂ ድሎች የተመዘገቡበት ወር ነዉ።የካቲት ወር ለኢትዮጵያዉያን፣ ለመላዉ አፍሪቃ ብሎም ለመላዉ ጥቁር ሕዝቦች ድል በደማቁ የታተመበት የዓድዋ ድል የተበሰረበት ወር ነዉ። በተለያዩ ሞያ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሞያዎቻቸዉ የዓድዋን ድል በተለያዩ ክንዉኖች በድምቀት ያከብራሉ፤ ያስባሉ። የዓድዋ ተጓዦች አድዋ ጉዞ ስድስት አካሂደዋል። አዲስ አበባ የሚገኙ ወደ 14 የሚሆኑ ሰዓልያን በበኩላቸዉ «ዝክረ ዓድዋ» በሚል በተለይ ታሪክን አጉልተዉ የሚሳዩበትን የሥነ-ጥበብ ሥራዎች ለተመልካች ማቅረባቸዉ በተሰናባቹ የፈረንጆቹ ዓመት ኑ ታሪካችንን እንይ «ዝክረ ዓድዋ » በሚል ርዕስ የዳሰስነዉ ርዕስ ነበር ።

Bete Israelis in Gondar
ምስል DW/G. Tedla

«ከባዱ ምልሰት»

የቤተ- እስራኤላዉያኑ ጉዳይ ሌላዉ የዳሰስነዉ ርዕሳችን ነበር ። በ2011ዓ.ም ማለትም ጥር ወር መገባደጃ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ለመሄድ ይጠባበቁ ከነበሩ ቤተ-እስራኤላዉያን መካከል ወደ ሰማንያ ሦስት የሚሆኑት ፈቃድ አግኝተዉ እስራኤል ገብተዋል። በኢትዮጵያ የቤተ- እስራኤላዉያንን ጉዳይ ተሟጋች አቶ መስፍን አሰፍ እንደነገሩን ከሆነ ደግሞ ወደ እስራኤል ለመሄድ በአዲስ አበባና በጎንደር በሚገኝ መጠባበቅያ ጣብያዎች የሚገኙ ቤተ-እስራኤላዉያን ወደ 13 ሺህ ይሆናሉ።

«ኪነ-ጥበብ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ»

Äthiopien Debebe Eshetu
ምስል Debebe Eshetu

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጥበብ ጋር ያላቸዉ ቅርበት ስልጣን ከያዙም በኋላ ከጥበቡ ጎራ አለመራቃቸዉ «ከሚያዝያ እስከ ሚያዝያ» በተሰኘዉ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ አንደኛ ዓመት በዓለ ሲመት ላይ በርካታ የጥበብ አፍቃሪዎች እና ከያኒዎች ተናግረዋል። በሚለኒየም አዳራሽ የነበረዉን ዝግጅት መድረክ የመራዉ አንጋፋዊ አርቲስት ደበበ እሸቱ በበኩሉ ሙዚቃ ቋንቋን ማወቅ አይጠይቅም ሁለተኛ ኢትዮጵያዊነት አማራጭ የማይገኝለት ነዉ ነበር ያለን።

ለመደሰት፣ ለመዝናናት፣ ለመቆዘም፣ በባዕድ ሀገር ሆኜ ሀገሬን፣ ቤተሰቤን፣ ባልንጀሮቼን ሁሉ ስናፍቅ መሸሸጊያዬ ይለዋል መጽሐፍን። በስደት ዓለም በጀርመን ሲኖር ወደ አምስት ዓመት የሆነዉ ወጣት ኢዮብ ዩናስ ነዉ። 

ማንበብ ትረካ ከልጅነቴ የነበረ ፍላጎት በመሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ዝግጅት ፍላጎቴን እንዳዳብር ረድቶኛል የሚለዉ ኢዮብ ኢትዮጵያ ሳለሁ መጽሐፍ እያነበብኩ ራሴን እየቀዳሁ በካሴት አስቀምጥ ነበር ሲል አስታዉሷል። አሁን ደግሞ ድምፁን እየቀዳ በተንቀሳቃሽ ምስል ጭምር በዩቲዩብ እና በሌሎች ማኅበራዊ መገናኛዎች ዘዴዎች በማሰራጨቱ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ታዋቂነትን አግኝቶአል።

«የ2019 የባህል መሰናዶ ቅኝት»

በጎርጎረሳዉያኑ 2019 ዓመት መጀመርያ ወር ማለትም በ2011 ዓም ጥር ወር አጋማሽ በድምቀት በአዊ ብሔረሰብ ዞን እንጅባራ ከተማ ለ79ነኛ በድምቀት የተከበረዉ የ7 ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር መረሃ ግብር በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ተጠይቆም ነበር። የፈረሰኞች ማኅበር የተመሰረተዉ አባት አርበኞች የጣልያንን ወራሪ ድል ከነሱ በኋላ መሆኑን የማኅበሩ ሊቀመበር አለቃ ጥላዬ በዚሁ በሚጠናቀቀዉ የጎርጎረሳዉያን 2019 መጀመርያ ለዶይቼ ቬሌ DW ተናግረዉ ነበር።

የባህል መድረክ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም መኖርያ በሆነዉ በሙጋቤ አገር ዚምባቤ መዲና ሃራሪ ላይ የሚገኘዉን የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት የተባለዉን የኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ምግብ ቤትንም አግኝቶ ጠይቋል።

«የደርግ ባለስልጣኑ እና ሃራሬ»

Äthiopien Fisseha Desta  und Erich Honecker (1969)
ምስል Privat

የንግሥት ማክዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራን ባለቤት ኢትዮጵያዊትዋ ናርዶስ ሌናርድት እንደነገረችን ቡና ቤት ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ ከጀመረ ወደ አራት ዓመት ሆነዉ። የዚምባቤ ሕዝብ በጣም ሰላማዊ ነዉ። የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ምግብ ቤቱን ጎብኝተዉ አያዉቁም። ነገር ግን በለቁሶ ቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ታይተዉ ያዉቃሉ ስትል የነገረችን በዚሁ በሚጠቃለለዉ የፈርንጆቹ ዓመት መጀመርያ ላይ ነበር። በሚቀጥለዉ የፈረንጆቹ 2020 ኮነሬል መንግሥቱን ኃይለማርያም ጋር ቃለ-ምልልስ አድርገን ይዘን ለመቅረብ የጀመርነዉን ጥረታችንን እንቀጥላለን ፤ ጥሪያችንን የሰሙት መንግሥቱም መልስ እንደሚሰጡን ተስፋ እናደርጋለን ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን!

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ