1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ1ኛ ዓመት የዮንቨርሲቲ ተማሪዎች ተሞክሮዋ

ዓርብ፣ ጥቅምት 15 2006

ኢትዮጵያ ውስጥ አጋጣሚዎች ካልፈቀዱ በስተቀር ከቤተሰብ ተለይቶ መኖር ብዙም አልተለመደም። ከነዚህ ከአጋጣሚዎች አንዱ ወጣቶች ለዮንቨርስቲ ትምህርት ወደ ሌላ ከተማ ተመድበው ሲሄዱ ነው።

https://p.dw.com/p/1A5gd
ምስል DW

ለመሆኑ የመጀመሪያ ዓመት የዮንቨርሲቲ ተማሪዎችን ምን ይጠብቃቸዋል? እንዴትስ ይወጡታል? ለትምህርት ከሚኖሩበት ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ተመድበው የተጓዙ ሶስት ወጣቶች በመጀመሪያ ዓመት የዮንቨርሲቲ ቆይታቸው ስለጠበቁት እና ስለ አገኙት አጫውተውናል። እዮሲያስ ማሞ ተወልዶ ያደገው በናዝሬት ከተማ ነው። የ18 ዓመቱ የምህንድስና ተማሪ ለትምህርት ወደ ደብረ ታቦር ከሄደ 2ኛ ሳምንቱን ይዟል። ከወላጆቹ ተለይቶ ለረዥም ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ሲሄድ የመጀመሪያ ጊዜው ነው። የሚማርበት ዮንቨርስቲ የመጀመሪያ ምርጫው አልነበረም። ቢሆንም በቦታው ደስተኛ ነው። የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎቹ ትምህርት ከጀመሩ ዛሬ አምስተኛ ቀናቸው ነው።

ሌላዋ ወጣት ቤተልሔም አጥናፉ ትባላለች። ለትምህርት ከድሬደዋ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው በመስከረም ወር መጨረሻ ነው። ወጣቷ ትናንት ምዝገባ ማጠናቀቃቸውን ነግራናለች። ትምህርት ገና አልተጀመረም። ምን እያረገች ነው? አጫውታናለች።

MStudenten auf dem Campus der Universität Addis Abeba
ምስል DW

እንደ ቤተልሔም ሁሉ ሀሰን ነገየ የድሬደዋ ልጅ ነው። የተመደበው ግን መቀሌ ከተማ ነው። ሀሰን ትምህርት ስላልተጀመረ ወደ ከተማ እንጂ ወደ ቤተ መፅሀፍት እስካሁን አልሄደም። ከሀገር ጉብኝት ሌላ የትምህርት ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

ሁሉም ወጣቶች ከሌሎች ተማሪዎች ጋ ማደሪያ ክፍል መጋራት ግድ ይላቸዋል። አብረው ሲኖሩ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም የእስካሁኑ የጋራ ህይወት ምን ይመስላል? በሰፊው ገልፀውልናል።

ተማሪዎች የትም ሀገር ይኖሩ የት ስለ ምግብ ሲጠየቁ ብዙውን ጊዜ የትምህርት ቤት ምግብ አይጣፍጠንም ይላሉ። ወጣቶቹ በምግብ አቅርቦቱ ደስተኛ ይሆኑ? ሌላስ ምን ፈተና ገጥሟቸው ይሆን? ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ