1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ14ኛው ታላቁ ሩጫ ተሳታፊዎች

ዓርብ፣ ኅዳር 19 2007

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓመት አንዴ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል። የዘንድሮው ማለትም 14ኛው የሩጫ ውድድር እንዴት አለፈ? አረንጓዴ እና ቀይ ቲሸርት ለብሰው ባለፈው እሁድ በሺ የሚቆጠሩ ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገነኙ ኢትዮጵያውያን ፣ አዲስ አበባ የሚኖሩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና

https://p.dw.com/p/1Dvgi
ምስል Jiro Mochizuki

ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሲሮጡ፣ አንዳንዶችም ዘና ብለው ሲራመዱ ተስተውለዋል።በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተዘጋጀው እና በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አካማይነት የተጀመረው የሩጫ ውድድር ባለፈው እሁድ ለ 14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።

ሩጫው ጤናማ ትውልድን ለመፍጠር፣ በታዳጊ እና በወጣቱ ዘንድ የስፖርት ፍቅርን ለማዳበር የታቀደ ነው። ባዩሽ እሸቴ ፣ ማህሌት ካሱ እና ሳሙኤል ዳኛቸው በዚህ በታላቁ ሩጫ የተሳተፉ ሶስት ወጣቶች ናቸው። አነጋግረናቸዋል። በዚህ ሩጫ በየዓመቱ የሚሮጠው ሰው ቁጥር ሲጨምር ተስተውሏል።በወንዶች የሩጫ ውድድር አዝመራው በቀለ በሴቶች ደግሞ ውዴ አየለው አንደኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል። በዚህ ውድድር ከጠንካራ አትሎቶች ባሻገር ምንም ልምምድ አድርገው የማያውቁ ሯጮች ተሳትፈዋል። የሩጫው አዛጋጅ ዓላማ ብዙ ነው፤ የዚህ ውድድር አዘጋጅ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አየለ ዋና ዋና የሚሉትን ጠቅሰውልናል።

Äthiopien Lauf in Addis Abeba
ምስል Jiro Mochizuki

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንዴት እንዳለፈ በአጭሩ አጠያይቀናል። ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ