1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2ቱ ጀርመናውያን ታጋቾች መለቀቅ

ረቡዕ፣ የካቲት 28 2004

ባለፈው ጥር 9 ቀን 2004 ዓ ም በአፋር ምድረ በዳ አርታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ የውጭ ተወላጆች የሆኑ 5 አገር ጎብኝዎች ፣ ማለትም 2 ጀርመናውያን፤ 2 የኦስትሪያ ዜጎችና አንድ የሃንጋሪ ተወላጅ

https://p.dw.com/p/14G59
ምስል picture-alliance/dpa


ባለፈው ጥር 9 ቀን 2004 ዓ ም በአፋር ምድረ በዳ አርታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ ከኢትዮጵያ መንግሥት ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ የውጭ ተወላጆች የሆኑ 5 አገር ጎብኝዎች ፣ ማለትም 2 ጀርመናውያን፤ 2 የኦስትሪያ ዜጎችና አንድ የሃንጋሪ ተወላጅ ሲገደሉ፤ ሌሎች 2 ጀርመናውያን ፣ በአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ARDUF) አማጽያን ፣ታፍነው ተወስደው ከቆዩ ወዲህ ትናንት መለቀቃቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።
የአማጽያኑ ድርጅት ዛሬ ባወጣው መገለጫ እንዳስታወቀው፤ ሁለቱን ሰዎች ትናንት በአፋር በረሃ ለጀርመን ኤምባሲ ባለስልጣናትና ለሀገር ሽማግሌዎች አስረክቧል። በዓለም ውስጥ በሞቃትነት ወደር የሌላቸው ከሚባሉት ጥቂት አካባቢዎች አንዱ በሆነው በአፋር በረሃ ስለቆዩትና አሁን ስለተለቀቁት ሁለት ጀርመናውያን ፤ የጀርመንም የኢትዮጵያም መንግሥታት ለጊዜው ያሰሙት ቃል የለም።

Äthiopien Wüste Danakil
ምስል picture-alliance/dpa

የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (ARDUF) በበኩሉ ፤ ስለለቀቃቸው ሰዎች ሁኔታው ያሳዘነው መሆኑን ባወጣው መግለጫ ላይ በመጥቀስ፤ ወደ ሀገራቸው በሰላም ይገቡ ዘንድ በጎ ምኞቱን ገልጿል። ድርጅቱ በመግለጫው ክዚህ ቀደም ሰዎቹን ደህንነታቸው ወደ ሚጠበቅበት ሥፍራ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ የኢትዮጵያ ፈደራል መንግሥትና የክልል ባለሥልጣናት በፈጠሩት መሰናክል ሳይሳክልኝ ቀርቷል ይላል ። በመጨረሻም ሰኞ የካቲት 26, 2004 ሰዎቹን በአፋር ክልል የሃገር ሽማግሌዎች በኩል ማስርከቡን ገልጿል ። ተዋጊዎቹ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ጥር 9 ቀን 2004 ዓም በኤርታሌ እሳተ ገሞራ አካባቢ ከተጋጩበት ጊዜ አንስቶ 2ቱ ጀርመናውያን ቱሪስቶች በአርዱፍ ጥበቃ ሥር መቆየታችውንም እስታውቋል ። በወቅቱ 16 የመንግሥት ወታደሮች መገደላቸውንና ሁለት ተዋጊዎቹም በኢትዮጰያ ወታደሮች መማረካቸውን ያስታወስው አርዱፍ በተኩስ ልውውጡ ወቅት ቡድኑ ንፁሀን ያላቸው አምስት አውሮፓውያን አገር ጎብኝዎች የተገደሉት የኢትዮጵያ ሃይላት በተከፈተ ተኩስ ነው ይላል ።

Äthiopien Landschaft in Provinz Afar Kamele durch die Wüste
ምስል picture-alliance/dpa

ከዚያን ጊዜ አንስቶም ሁለቱን ጀርመናውያን በአፋር ክልል ሲንከባከብ መቆየቱን ነው መግለጫው የሚያስረዳው ። ታጋቾቹን ይቅርታ መጠየቁን በመግለጫው የጠቀሰው አርዱፍ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ሊለቃቸው መሞከሩንም አስታውቋል ። በአርዱፍ መግለጫ መሠረት ይህ ሙከራው በድርጅታችን ላይ ጦርነት አውጇል ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው አንድ ወር በአካባቢው ማናቸውንም እንቅስቃሴዎችን በማገዱ ምክንያት ሊሳካ አልቻለምም ብሏል ። የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የአረዱፍን ትግል ማክሸፍ ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ኤርትራን ለመወንጀል ይጠቀሙበት ነበርም ሲል ግልጿል ቡድኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አርዱፍ የሚባለው ድርጅት እጎአ በ1978 መመስረቱን አስታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ