የ2011 የዓለም የኤድስ ቀን ዘገባ
ሐሙስ፣ ኅዳር 21 2004ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግስታት የኤድስ መከላከያ መርሃ ግብር በዚሁ ዓመት የHIVን ስርጭት ለመግታት በተደረገው ጥረት አመርቂ ውጤት መገኘቱን አመልክቷል ። ለዚህም ዘገባው በምክንያትነት ከጠቀሳቸው ውስጥ አንዱ ከሁሉም በተለይ አብዛኛዎቹ የ HIV ተጠቂዎች በሚገኙበት በአፍሪቃ ለኤድስ ህሙማንና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት መሻሻሉ ነው ። የዶቼቬለው Gudrun Heise ባለፈው ሰኞ ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ይፋ የሆነውን ይህን ዘገባ በአጭሩ ቃኝቶታል ።
እ.ጎ.አ የ 2011 የዓለም የኤድስ ዘገባ በጥቅሉ በዓለም ዙሪያ በ HIV የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን ማብሰሩ እንደ አንድ በጎ ውጤት የሚታይ ነው ። ይሁንና አሁንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ በርካታ የችግሩ ተጠቂዎች ባሉባቸው ሃገራት ለኤድስ ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የበሽታው ስርጭትና የግንዛቤ እጥረት ማሳሰቡ አልቀረም ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከመካከላቸው አንዳንዶች አነጋግሯል ። የባለሞያ አስተያየትም ጠይቋል ።
ሂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ