1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2012 ዓም የኢትዮጵያ እቅዶችና ተግዳሮቶቻቸው 

እሑድ፣ መስከረም 11 2012

2012 ሃገሪቱ አጠቃላይ ምርጫ የምታካሂድበት ዓመት ነው። የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ፣ የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ እንዲሁም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ዐበይት ከሚባሉት የዓመቱ እቅዶች መካከል ይጠቀሳሉ።የዛሬው እንወያይ በ2012 ዓም በኢትዮጵያ በፖለቲካው እና በኤኮኖሚው ዘርፍ ሊከናወኑ የታቀዱ ጉዳዮችን እና እንቅፋቶቹን ይቃኛል።

https://p.dw.com/p/3Q1WN
Äthiopien - Weltrekord im Bäume pflanzen -Symbolbild
ምስል picture-alliance/G. Hellier

የ2012 ዓም የኢትዮጵያ እቅዶችና ተግዳሮቶቻቸው 

ኢትዮጵያ 2011ን ሸኝታ አዲሱን 2012ን ከተቀበለች ሁለተኛ ሳምንቷን አገባደደች።ኢትዮጵያውያን 2012ን በደስታ እና በተስፋ ቢቀበሉትም በአዲሱ ዓመት የሚያሰጓቸው ፣የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች ጥቂት እንዳይደሉ መረዳት አያዳግትም።2011 ሃገሪቱ በፖለቲካው በኤኮኖሚው እና በማህበራዊው ዘርፍ ብርቱ ፈተና ውስጥ የነበረችበት ዓመት ነበር።በዓመቱ ዜጎች ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል፤በግጭት እና በኹከት የበርካቶች ህይወት አልፏል።ሰላም የደፈረሰባቸው፣የደህንነት ስጋት ውስጥ ያለፉ አካባቢዎችም ነበሩ። የኑሮ ውድነት ህዝቡን አሰቃይቷል። ችግሩ አሁንም ብሶ ቀጥሏል። 2012 ሃገሪቱ አጠቃላይ ምርጫ የምታካሂድበት ዓመት ነው። የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ፣ የህዝብ እና የቤቶች ቆጠራ እንዲሁም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ዐበይት ከሚባሉት የዓመቱ እቅዶች መካከል ይጠቀሳሉ።የዛሬው እንወያይ በ2012 ዓም በኢትዮጵያ በፖለቲካው እና በኤኮኖሚው ዘርፍ ሊከናወኑ የታቀዱ ጉዳዮችን እና እንቅፋቶቹን ይቃኛል።ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል።እነርሱም ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ፣ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ጀርመን የሚኖሩ የኤኮኖሚ ምሁር እንዲሁም አቶ ገረሱ ቱፋ የፖለቲካ አቀንቃኝ ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ