1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2013 የዓለም ምርጥ የእግር ኳስ ስፖርተኞች መሸለም

ረቡዕ፣ ጥር 7 2006

የስጳኛውያኑ የሬአል ማድሪድ የእግር ኳስ ክበብ አጥቂ ፖርቱጋላዊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2013 ምርጥ የወንዶች እግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ የወርቅ ኳስ ተሸለመ።

https://p.dw.com/p/1AqWY
Preisverleihung Weltfußballer 2013 Cristiano Ronaldo
ምስል Fabrice Coffrini/AFP/Getty Images

የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ፊፋ ትናንት በስዊትዘርላንድ ባካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ሌላ፣ በሴቶች የጀርመን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ግብ ጠባቂ ናዲን አንገረርም ምርጥ ተጫዋች ተብላ የወርቅ ኳስ ሲሸል,ም፣ ጀርመናውያኑ ዩፕ ሀይንከስ እና ሲልቪያ ናይድ ደግሞ በወንዶች እና በሴቶች የእግር ኳስ ቡድን እጅግ ጥሩ አሠልጣኞች ብሎ ሸልሞአቸዋል። በተያያዘ ዜና፣ ትናንት ደቡብ አፍሪቃ ከሊቢያ ጋ የተጋጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በሊቢያ 2-0 ተሸንፎዋል።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ