1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የHIV ምርመራ ሳምንት በድሬዳዋ

ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2001

በድሬዳዋ መስተዳድር በዚህ ሳምንት ስለ HIV ስርጭትና የመከላከያ መንገዶች የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በፈቃደኘት ላይ የተመሰረተ ምርመራም እየተካሄደ ነው ።

https://p.dw.com/p/H4y5
..ይመርመሩ ራስዎን ይወቁ ....ምስል AP

በዚሁ ሳምንትም በርካታ ነዋሪዎች በደማቸው ውስጥ HIV መኖር አለመኖሩን ለማወቅ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደ ተዘጋጁት ቦታዎች በመምጣት በፈቃደኝነት ይመረመራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመስተዳድሩ በተለይ በገጠሩ አካባቢ በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል ይረዳል ብሎ ባመነው መሰረት ጋብቻዎች ከመፈፀማቸው በፊት የHIV ምርመራ መካሄዱ እንደ አንድ ቅድመ ግዴታ ተደንግጓል ። በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ጅቡቲና ሶማሌላንድ መካከል የድንበር ተሻጋሪ የ HIV ክትትል ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ከድሬዳዋ ዘግቧል ።