1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የICASA ጉባኤ ያነሳቸው ዐበይት ጉዳዮች

ረቡዕ፣ ኅዳር 27 2004

16 ተኛው የአፍሪቃ የኤድስ ና የአባለዘር በሽታዎች ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ አዲስ አባባ ውስጥ እንደቀጠለ ነው ። ጉባኤው ከተነጋገረባቸው ጉዳዮች ውስጥ ለጋሽ ሃገራት ለኤድስ መከላከያ መርሃ ግብር ለመስጠት ቃል የገቡት ገንዘብ ሊቀንስ የመቻሉ ስጋት አንዱ ነው ።

https://p.dw.com/p/S0ah
ምስል picture-alliance/dpa

ለጋሾች ቃል የገቡትን ገንዘብ እንዲሰጡ ከማሳሰቡ እና ከመከራከሩ ጎን ለጎን አፍሪቃውያን ለገንዘቡ ችግር የራሳቸውን መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባቸው ተገልጿል ። ጉባኤው የተነጋገረበትን ይህንና ሌሎች አሳሳቢ ችግሮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማውያን ይደርሳባቸዋል የሚባለውን መገለል አስመልክቶ የጉባኤው ተሳታፊ የሆኑትን ዶክተር ትዕግስት ግርማ የአፍሪቃ የህክምናና የምርምር ተቋም በንግሊዘኛው ምህፃር አምሬፍ(AMREF) ዋና ሃላፊ ን ሂሩት መለሰ በስልክ አነጋግራቸዋለች ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሸ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ