1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩሮ 2016 እና ስርዓተ አልበኛነት

ሰኞ፣ ሰኔ 6 2008

በፈረንሳይ ባለፈው ዓርብ በተከፈተው የአውሮጳ እግር ኳስ ቻምፒዮና ግጥሚያ ከትናንት በስቲያ በማርሴይ ከተማ በእንግሊዝ እና በሩስያ መካከል በተደረገው ጨዋታ የሁለቱ ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድኖች ደጋፊዎች ፣ ብዙዎቹም በመጠጥ ኃይል የተገፋፉ፣ በቀሰቀሱት ሁከት በርካቶች መቁሰላቸው ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/1J5tU
Frankreich Marseille UEFA Euro 2016 Stadion Fans Ausschreitungen
ምስል picture-alliance/empics/PA Wire/N, Potts

[No title]

ይህን ተከትሎ አንዳንድ ደጋፊዎች ታስረዋል፣ አንዳንዶችም ለፍርድ ይቀርባሉ። አንድ የሩስያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊ ከፈረንሳይ እንዲወጣም ታዞዋል። የፈረንሳይ ሀገር አስተዳደር ሚንስቴር አንዳንድ ርምጃዎች የወሰደ ሲሆን፣ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ማኅበር ደግሞ በእንግሊዝና በሩስያ ደጋፊዎች መካከል ረብሻዉ ከቀጠለ እንግሊዝ እና ሩስያ ከእግር ኳስ ግጥሚያዉ ሊታገዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል።

ሀይማኖት ጥሩነህ


አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ