1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴትስ፤ ግድያና አፀፋ ግድያ

ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2008

ነጭ ፖሊሶች ሰሞኑን ሁለት ጥቁሮችን መግደላቸዉ ያስቆጣቸዉ ታጣቂዎች ዳላስ ዉስጥ በፖሊስ ላይ በከፈቱት የበቀል ተኩስ አምስት ፖሊስ ገድለዉ ስድስት አቁስለዋል።በተለያዩ ከተሞች የሚኖረዉ ሕዝብ ደግሞ በየአደባባዩ በመሠለፍ የነጭ ዘረኛ ፖሊሶችን እርምጃ አዉግዟል

https://p.dw.com/p/1JLvQ
ምስል picture-alliance/dpa/M. R. Olivas/The Dallas Morning News

[No title]

የዩናይትድ ስቴትስ ነጭ ፖሊሶች የሐገሪቱን ጥቁር ዜጎች በተደጋጋሚ መግደላቸዉ የጫረዉ ቁጣ፤ ተቃዉሞና አፀፋ እርምጃ የዓለም ልዕለ ሐያሊቱን ሐገር ግራ ቀኝ እያላጋት ነዉ።ነጭ ፖሊሶች ሰሞኑን ሁለት ጥቁሮችን መግደላቸዉ ያስቆጣቸዉ ታጣቂዎች ዳላስ ዉስጥ በፖሊስ ላይ በከፈቱት የበቀል ተኩስ አምስት ፖሊስ ገድለዉ ስድስት አቁስለዋል።በተለያዩ ከተሞች የሚኖረዉ ሕዝብ ደግሞ በየአደባባዩ በመሠለፍ የነጭ ዘረኛ ፖሊሶችን እርምጃ አዉግዟል።የሐገሪቱ ፖለቲከኞች እየተካረረ የመጣዉን ግጭትና ግድያ ለማቀዝቀዝ እየሞከሩ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለስ