1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪና የኤርትራ መልስ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2003

ዩናይትድ ስቴትስ የኤርትራ መንግሥት በሃገሪቱ ውስጥ ስላለው የድርቅና የረሃብ አደጋ ለዓለም ማህበረሰብ ተጨባጭ መረጃ እንድታቀርብ ጠየቀች ።

https://p.dw.com/p/RbD9
ምስል AP Graphics/DW

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ማክሰኞ እንደተናገሩት ኤርትራ ሁኔታውን በግልፅ ማሳወቋ ሊደርስ የሚችል አስከፊ አደጋን ለመቋቋም ይረዳል ። ኤርትራ በበኩሏ በሀገርዋ የረሃብና የድርቅ አደጋ እንዳልተከሰተ ፣ ቢከሰት እንኳን ችግሩን ለመቋቋም የሚያስችል በቂ አቅም አለን ስትል አስታውቃለች ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኤርትራ ፕሬዝዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ አማካሪ አቶ የማነ ገብረ አብ በኤርትራ እስካሁን የሚያሰጋ ሁኔታ የለም ብለዋል ። አሜሪካን ለኤርትራ ህዝብ ካሰበችም የሚጠበቅባት የኤርትራን የልማት እቅድ መደግፍና በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳት የመሳሰሉትን እርምጃዎች መውሰድ መሆኑን አቶ የማነ ተናግረዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ