1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የዩኤስ አፍሪቃ ረዳት ሚኒስትር

ሰኞ፣ ነሐሴ 29 2009

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ዶናልድ ያማማቶ የአፍሪቃ ረዳት ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። አምባሳደር ያማማቶ አዲስ ለተሾሙለት ቢሮ ነገ ሥራ ይጀምራሉ። ያማማቶ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለሶስት አመታት በአምባሳደርነት አገልግለዋል። በጁቡቲም አምባሳደር ሆነው ያውቃሉ።

https://p.dw.com/p/2jLI5
USA US-Außenministerium in Washington - Siegel
ምስል picture-alliance/dpa/T. Brakemeier

የዶናልድ ያማማቶ ሹመት

የአሜሪካ መንግሥት የዲፕሎማሲ ማዕከል ድረ-ገፅ እንደሚጠቁመው አምባሳደሩ ከጎርጎሮሳዊው 2003 እስከ 2006 ዓ.ም. በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር የአፍሪቃ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው አገልግለዋል። አፍሪቃን ችላ ብሏል እየተባለ የሚወቀሰው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቦታው ሌሎች ሁለት እጩዎች ለመሾም ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቶ ነበር።


መክብብ ሸዋ 
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ