1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ እና የዓለም አቀፍ የጸጥታ ጉባዔ

ሰኞ፣ የካቲት 2 2001

በጀርመን በሚውንኽን ከተማ በተካሄደውና ትናንት ማምሻውን በተጠናቀቀው ዓለም አቀፍ የጸጥታ ጉባዔ ላይ የተገኙት የዩኤስ አሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደን በፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የሚመራው አዲሱ የሀገራቸው መንግስት ዓለም አቀፍ ትብብርን የሚያዳብር የውጭ ፖሊሲ ለመከተል ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ፤ በተለይ ሩስያን እና ኢራንን በተመለከተ።

https://p.dw.com/p/GqLr
ያሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደን
ያሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደንምስል AP

ነገር ግን፡ ዩኤስ አሜሪካ በተለይ በአፍጋኒስታን በታሊባን አንጻር በምታካሂደው ውጊያ ላይ ከተጓዳኞችዋ ሀገሮች ብዙ ትብብር እንደምትጠብቅ ባይደን በዚሁ ጊዜ አክለው አስረድተዋል። ይልማ ሀይለሚካኤል

AA, SL