1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ እና የገጠማት የወጪ ቁጠባ ውዝግብ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 21 2003

የፊናንስ ጠበብት እንደሚሉት፡ በዩኤስ አሜሪካ የውጭ ዕዳ ጣራን ከፍ በማድረጉ ጥያቄ ላይ ዴሞክራቶች እና ሬፓብሊካውያን ስምምነት ላይ ባይደርሱ፣ ሀገሪቱ እስካሁን እንደተገለጸው እአአ እስከ ነሀሴ ሁለት 2011 ድረስ ሳይሆን እስከ ነሀሴ አስር ድረስ ዕዳ የመክፈል አቅሟ እንደተጠበቀ ይቆያል።

https://p.dw.com/p/RcrC
ምስል dapd

እስካሁን የውጭ ዕዳው ጣራ 14,3 ትሪልየን ዶላር ሲሆን፡ ይህ መጠን ከፍ ካላለ የውጭ አበዳሪዎችን መክፈል ቀርቶ በሀገርም ውስጥ ብዙ ክፍያዎችን ማከናወን አትችልም። እርግጥ፣ ባጠቃላይ ዩኤስ አሜሪካ ክስረት ያጋጥማታል ተብሎ አይታሰብም። ይሁንና፣ የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ኡልሪከ ረመር እንደማያውቅ እንደዘገበችው፡ ዋሽንግተን ውስጥ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው የአቋም ልዩነት እንዲህ እንዳሁኑ ተካሮ አያውቅም።

ኡልሪከ ረመር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ