1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩጋንዳ፣ የተቃዉሞ ሠልፍና የፀጥታ አስከባሪዎች እርምጃ

ረቡዕ፣ ግንቦት 3 2003

ሐገሪቱን ለሃያ-ስድስት አመታት የገዙት ፕሬዝዳት ዩዌሪ ሙሳቬኒ ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን በዓለ ሲመታቸዉን ለማክበር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ግብዣ ደግሰዋል

https://p.dw.com/p/RNLf
ካምፓላ-አመፁምስል dapd

የኑሮ ዉድነት፥ ሥራ አጥነትና ድሕነት የጠናበት የዩጋንዳ ሕዝብ የሐገሪቱን መንግሥት በመቃወም አደባባይ ወጥቶ ነበር።የሰሜን አፍሪቃዉ አይነት ሕዝባዊ አመፅ ይገጥመኛል ብሎ የሰጋዉ የሐገሪቱ መንግሥት ግን በሠልፈኛዉ ላይ ጠንካራ እርምጃ አስወስዷል።ፀጥታ አስከባሪዎች ሠልፈኛዉን በአስለቃሽ ጋዝና በዉሐ በትነዉታል።ሕዝቡ በኑሮ ዉድነት መሰቃየቱን በሚናገርበት ባሁኑ ወቅት ሐገሪቱን ለሃያ-ስድስት አመታት የገዙት ፕሬዝዳት ዩዌሪ ሙሳቬኒ ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን በዓለ ሲመታቸዉን ለማክበር የአንድ ሚሊዮን ዶላር ግብዣ ደግሰዋል።ሲሞነ ሽላይድቫይን የዘገበችዉን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል።

ሲሞነ ሽልንድቫይን

ይልማ ሐ/ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ