ያለ ሾፌር የሚነዱ መኪናዎች

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:27 ደቂቃ
10.08.2016

ያለ ሾፌር የሚነዱ መኪናዎች

በአንዳንዶቹ ያለ ሾፌር የሚነዱ መኪናዎች ላይ በቅርቡ በጎዳናዎች ላይ ሙከራ ሲካሄድ የሞት አደጋ መድረሱ፤ ሰዉ በመኪናዎቹ ላይ እምነት እንዳይኖረው እያደረገ መጥቷል ።


በአሁኑ ጊዜ ብዙ የሚነገርላቸውን ፣ ሾፌር አልባ መኪኖች የመሥራት ሙከራ የተጀመረው በጎርጎሮሳዊው 1920 ዎቹ ሲሆን ተስፋ ሰጭ ሙከራዎች የታዩት ደግሞ በ1950 ዎቹ ነበር ። ያላሽከርካሪ መሄድ የሚችል መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ ተሠርቶ የቀረበው ደግሞ በ1980 ዎቹ ነው ። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ዋና ዋና የሚባሉት የአውቶሞቢል ኩባንያዎች እና የምርምር ተቋማት በየጊዜው የተሻሻሉ ያለ ሾፌር የሚሽከረከሩ የተለያዩ መኪናዎችን አምርተዋል ። ከእነዚህ መኪናዎች በአንዳንዶቹ ላይ በቅርቡ በጎዳናዎች ላይ ሙከራ ሲካሄድ የሞት አደጋ መድረሱ፤ ሰዉ በመኪናዎቹ ላይ እምነት እንዳይኖረው እያደረገ መጥቷል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

ከማዕቀፉ ተጨማሪ ዘገባዎች

ተከታተሉን