1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአስራ አንድ አመቷ የተዳረችው ማሚት ሐብቱ

ሐሙስ፣ ጥር 4 2009

ያለ ዕድሜ ጋብቻ በኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንስም፣ አሁንም ከአምስት ሴት ህፃናት ሁለቱ ያለፍላጎታቸው ሶስት ጉልቻ እንደሚመሰርቱ «ገርልስ ኖት ብራይድስ» የተሰኘው የግብረ-ሰናይ ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።

https://p.dw.com/p/2Vi3r
Äthiopien Opfer von Kinderehen in Mekelle
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

Ber. Melkelle(Victim of forced marriage) - MP3-Stereo

ድህነት፣የትምህርት እና ኤኮኖሚያዊ አማራጮች እጦት ወላጆች ልጆቻቸውን በግዴታ ለመዳር ከሚያስገድዷቸው ጉዳዮች መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን የግብረ-ሰናይ ድርጅቱ መረጃ ያትታል። በኢትዮጵያ ወንዶችም ሆነ ሴቶች ትዳር ለመመሥረት 18 ዓመት ሊሞላቸው እንደሚገባ ሕግ ቢደነግግም፣ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እኩል ተግባራዊ አይደረግም። 15 ዓመት ሳይሞላቸው የሚዳሩ ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እድላቸው አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር የሰብዓዊ ጥሰትም ይገጥማቸዋል። ወደ መቀሌ የተጓዘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር በ11 አመቷ በግዴታ የተዳረችውን ማሚት ሐብቱን አግኝቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።  
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ