1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያልተመጣጠነ የምክር ቤት መቀመጫ በድሬዳዋ

ሐሙስ፣ መጋቢት 2 2013

በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በከተማ እና በገጠር ለሚኖረው ሕዝብ የተሰጠው የመቀመጫ ክፍፍል ተገቢ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ/ኢዜማ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።

https://p.dw.com/p/3qUfi
Äthiopien Dire Dawa | Administration Council
ምስል Mesay Tekelu/DW

ተፎካካሪዎች ችግሩ እንዲፈታ ጥረት እንደሚያደርጉ ዐስታውቀዋል

በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በከተማ እና በገጠር ለሚኖረው ሕዝብ የተሰጠው የመቀመጫ ክፍፍል ተገቢ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ/ኢዜማ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ምክር ቤቱ ካለው 189 ከአንድ መቶ በላይ የሚሆነውን መቀመጫዎች ለገጠር ቀሪውን ለከተማ የሰጠ ነው። ኢዜማ እና አብን በቀጣይ በምርጫው አሸንፈው ምክር ቤት በመግባት ይህ ችግር እንዲፈታ ጥረት እንደሚያደርጉ ዐስታውቀዋል።

በዘጠኝ የከተማና ሰላሳ ስምንት የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረው የድሬደዋ አስተዳደር በም/ቤቱ ካለው አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ መቀመጫ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆነውን ለገጠር ቀሪውን ለከተማ እጩ ተወዳዳሪዎች የሰጠ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ/ኢዜማ ድሬደዋ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ወንደሰን አሰፋ ይህ ኢፍትአዊ ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ሰብሳቢ አቶ የሺጥላ ማሞ በተመሳሳይ ክፍፍሉ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡አቤቱታ ቢያቀርቡም መፍትሄ ባለማግኘታቸው በቀጣይ ምክር ቤት ገብተው ለመታገል መወሰናቸውን አስረድተዋል።

እስካሁን ከአርባ በላይ እጩዎችን ያስመዘገባው ኢዜማም በዚህ ምርጫ መፍትሄ አላገኘም ላለው ኢፍትሀዊነት በቀጣይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ገልፃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ ያሲን የዘንድሮው ምርጫ ቀደም ሲል በነበሩ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሁለቱ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ሰኔ ወር በመስተዳድሩ ለሚካሄደው ምርጫ ለመሳተፍ እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል።

መሣይ ተክሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ