1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያዳጊ ሀገሮች የድህነት ቅነሳ ጥረት

ዓርብ፣ መጋቢት 28 2004

በመልማት ላይ ባሉ ሀገሮች ዉስጥ የሚታየዉን ድህነት በመቀነሱ ረገድ የግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ሚና ሊይዝ እንደሚገባ የጀርመን የኢኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስትር ድርክ ኔብል አስታወቁ። ሚንስትሩ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት፣ በአዳጊ አገራት ዉስጥ ወረት ለሚንቀሳቀበት ተግባር

https://p.dw.com/p/14YVg
ምስል Fotolia/Luftbildfotograf

በመልማት ላይ ባሉ ሀገሮች ዉስጥ የሚታየዉን ድህነት በመቀነሱ ረገድ የግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ሚና ሊይዝ እንደሚገባ የጀርመን የኢኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስትር ድርክ ኔብል አስታወቁ። ሚንስትሩ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት፣ በአዳጊ አገራት ዉስጥ ወረት ለሚንቀሳቀበት ተግባር ዋስትና መስጠቱ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል። በመልማት ላይ ባሉ ሀገሮች ዉስጥ የሚታየዉን ድህነት በመቀነሱ ረገድ የግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ትልቅ ሚና ሊይዝ እንደሚገባ የጀርመን የኢኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስትር ድርክ ኔብል አስታወቁ። ሚንስትሩ ለ DW በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት፣ በአዳጊ አገራት ዉስጥ ወረት ለሚንቀሳቀበት ተግባር ዋስትና መስጠቱ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል።

በአለም በብዙ አዳጋ ሀገሮች ዉስጥ የሚታየዉን ድህነት በግማሽ ለመቀነስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያስቀመጠዉን የምትዕአመቱን የልማት ግብ በተመለከተ ትልቅ እርምጃ መደረጉን የአለም ባንክ ከጥቂት ግዜ በፊታ ያወጣዉ አንድ መዘርዝር አሳይቶአል። ይህ በርግጥ አበረታች ዜና ቢሆንም በመልማት ላይ ያሉ አገሮች በዚሁ ተረጋግተዉ ኢኮነሚያዊ እድገት ለማስገኘት የጀመሩትን ጥረት ችላ ማለት እንደማይገባቸዉ የጀርመን የኢኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስትር ድርክ ኔብል አሳስበዋል።

«እኔ እንደማምነዉ፣ አዳጊ ሀገሮች ድህነትን ለመቀነስ የሚያደርጉት ጥረት ዉጤት ያስገኝ ዘንደ ኢኮነሚኢዊ እድገት ወሳኝ ነዉ። ይህ ገሃድ እንዲሆንም አስፈላጎዉን ቅድመ ግዴታ ሊሟላ ይገባል። የወረት ከወች የሚገባዉ የካፒታል እንቅስቃሴን ጭምር የሚያስተካክል ሕግ ሊኖር ይገባል። ፀረ- ሙስና ትግሉ ለኢንቬስትመንት የሚሰጠዉ ዋስትናም እኩል ትኩረት ማግኘት አለባቸዉ። የካፒታል ፍሰት የስራ ቦታ ሊፈጥር ፣ ይህም ሕዝብን ከድህነት ሊያላቅቅ ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ለሕዝብ አስፈላጊዉን የጤና፣ የትምህርት ወይም የመሠረተ ልማት አገልግሎትን ማቅረብ የሚያስችለዉን ግብር ያስገኝለታል።»

Kongo Nahrung in den Least Developed Countries Flash-Galerie
ምስል Dagmar Wittek

የምትዕአመቱ የልማት ግብ ሃሳብ ከአስር አመታት በላይ በፊት በቀረበበት ግዜ የበለፀጉ አገሮች እንደ አዉሮጳዉያን ዘመን አቆጣጠር እስከ 2015 ድረስ ለአዳጊ አገሮች ከጠቅላላ ብሄራዊ ገብያቸዉ 0,7 ከመቶ ለመስጠት ቃል መግባታቸዉ የሚታወስ ነዉ። ይሁንና አለማቀፉ የኢኮነሚ ልማት ትብብር ድርጅት በምህጻሩ OECD የአደጉት አገሮች ይህንን ቃላቸዉን በተባለዉ ግዜ መጠበቃቸዉን አብዝቶ እንደሚጠራጠረዉ ገልጾአል። ያም ቢሆን ግን የጀርመን የኢኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስትር ድርክ ኔብል ምንም እንኳ በአለም የሚታየዉ የፊናንስ ቀዉስ ይህንኑ ቃል የመጠበቁ ተግባር አዳጋች ቢያደርገዉም አገራቸዉ ጀርመን ቃልዋን ለመጠበቅ አስፈላጊዉን ቅድም ዝግጅት አድርጋለች።

«የጀርመን የኤኮነሚ ተራድኦ ሚንስቴርን በጀት በ 2010፣ 2011 እና 2012 ዓ,ም በተከታታይ አሳድገናል። የመንግስት የልማት ሰጭ ድርጅቶችን ሥራ በተሻለ መንገድ ለማቀናበር እና በተመደበላቸዉም ገንዘብ ብዙ ዉጤት ለማስገኘት በማሰብ የመዋቅር ማስተካከያ አድርገናል።»

ከዚህ በተጨማሪም ጀርመናዊዉ ሚኒስትር ድርክ ኔብል እንደገለጹት ድህነትን በመታገሉ ረገድ ወሳኝ ሚና ለያዘዉ የአየር ንብረት ለዉጥ የሚያስከትለዉን መዘዝ ለመታገሉ እርምጃ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠችዉ ጀርመን አዳጊ አገሮች እንደ በ2015 ዓ,ም አዳጊ አገሮች የምትዐመቱን የልማት ግባቸዉን ያሳኩ ዘንድ እስካለፈዉ አመት ድረስ የሰጠችዉ የልማት እርዳታ ምንም እንኳ ጀርመን ያስገኘችዉ አመታዊ ኢኮነሚኢዊ እድገትዋ 3ከመቶ ብቻ ቢሆንም 0,4 ከመቶ ደርሶአል።

አርያም ተክሌ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ