1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያፍሪቃውያኑ ተገን ጠያቂዎች ችግር በሞልታ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 5 2004

የአውሮጳ ህብረት አባል መንግሥታት፡ የህብረቱ ምክር ቤት እና ኮሚሽን የህብረቱን አባል ሀገራት የተገን አሰጣጥ ፖሊሲ አንድ ወት ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እያካሄዱ ነው። ይሁንና፡ በብራስልስ ውይይቱ በቀጠለበት ባሁኑ ጊዜ፡ ወደ አውሮጳ የጠረፍ ሀገራት የሚገቡት

https://p.dw.com/p/15Vk8
Titel: Asylbewerber in Malta Asylbewerber in Malta 20/06/2012. Eine Gruppe von Asylbewerber quatschen am Zaun 20/06/2012. Die Rechte gehören Laurens Cerulus, einem Korrespondenten der DW. Er hat uns die Rechte gegeben, seine Bilder auf dw.de zu veröffentlichen.
ምስል Laurens Cerulus

ተገን ጠያቂዎች የሚያጋጥማቸው ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል። ሞልታ ትንሿ የህብረቱ ሀገር ብትሆንም፡ ከሌሎች አባል ሀገራት ጋ ሲነፃፀር ብዙ ተገን ጠያቂ የሚገባባት ሀገር ናት። በመሆኑም፡ የሞልታ መንግሥት ስደተኞቹን ማስተናገድ የሚችልበት ተጨማሪ ርዳታ እንዲቀርብለት ጠይቋል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተገን ጠያቂዎቹ የሚገኙበት ሁኔታ ኢሰብዓዊ ሲሉ ነቅፈዋል።

በቫሌታ ቱሪስቶች ሲዝናኑ ቢታይም፡ ሀገሪቱ በወቅቱ ብዙ አጣዳፊ ችግሮች እንደተደቀኑባት ለማንም ግልጽ ነው።
በሜድትሬንየን ባህር የምትገኘዋ ደሴት ሞልታ ከሕዝቧ የሚበልጥ ተገን ጠያቂ እንደምታስተናግድ መንግሥታዊ ያልሆነው የጀዚዊት የስደተኞች አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አባል የሆኑት ካትሪን ካሚሌሪ እንዳስታወቁት፡ በሞልታ ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ ብዙ ለውጥ ታይቶዋል።
« ለፉት አሥር ዓመታት ብዙ ስደተኞች በጀልባ ሲመጡ አይተናል። እና ባለፉት አሥር ዓመታት በሞልታ የስደተኞቹ ሁኔታ በጣም ተባብሶዋል። »
ሀገሪቱ በአማካይ በዓመት 1,500 ተገን ጠያቂዎችን ትቀበላለች፤ ካለፈው ጥር ወር ወዲህ እንኳን 900 ስደተኞች ከሊቢያ መዲና ትሪፖሊ በጀልባ ሞልታ የገቡ ሲሆን፡ ብዙዎቹ ከአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት የሄዱ ናቸው። ከነዚህም እስከ 60 ከመቶ የሚሆኑት ዓለም አቀፍ ከለላ እንደሚያስፈልጋቸው ቢረጋገጥም፡ የሞልታ መንግሥት ተገን ጠያቂዎቹን ከውጭ በሚቆለፉ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በቁጥጥር ያዋለበት፡ እንዲያውም አንዳንዶቹን እስከ አንድ ዓመት ተኩል የሚያስርበት ፖሊሲው ብርቱ ወቀሳ አስከትሎበታል። ስደተኞቹ ያስገቡት ተገን ማመልከቻቸው መልስ እስኪያገኝላቸው ለብዙ ወራት በሳፊ እስር ቤት ሁለት መቶ አልጋዎች በተዘረጉባቸው የዕቃ መጋዘኖች ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ መኖር መገደዳቸውን ነው የሚናገሩት።
« የተሻለ ኑሮ ፍለጋ እዚህ ሞልታ መጥተናል፤ ነፃነቴን ወደማገኝበት ሌላ ቦታ መሄድ እፈልጋለሁ። እዚህ ጥሩ አይደለም። »
ስደተኞቹ ከመጠለያ ጣቢያው ውጭ የትም ሊሄዱ አይፈቀድላቸውም። እንዲያውም ክፍላቸው ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደሚውሉ ነው የሚናገሩት።
« በዚህ ማዕከል ውስጥ ከአንድ ዓመት ከሦስት ወር በላይ ሆኖናል። እስካሁን ከአንድ ልብስ በስተቀር የሰጡን ነገር የለም። ውጭ መውጣት አንችልም፤ ከአንድ ዓመት ተኩል ወዲህ ይኸው ሀያ አራት ሰዓት ሙሉ ከክፍላችን አልወጣንም፤ ታመናል። ሙቀቱ ኃይለኛ ነው። »
የተገን ጠያቂዎቹን የኑሮ ሁኔታ ያላሻሻለው የሞልታ መንግሥት የአውሮጳ ህብረት ስደተኞቹ ብዛት የገጠመውን ችግር ማቃለል የሚችልበትን ርዳታ እንዲያቀርብለት ጥሪ ማሰማቱን በሞልታ የፍትህ እና የሀገር አስተዳደር ሚንስቴር ውስጥ የፖሊሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ጆሴፍ ሴይንት ጆን አስታውቀዋል
« በተለይ አንድ የጋራ የአውሮጳ ህብረት የተገን አሰጣጥ ፖሊሲ ለማውጣት እየሰራን የምንገኝበት ሁኔታ እርስ በርስ መረዳዳት እንደሚገባን የሚያበረታታ ርምጃ መሆኑን በማስረዳት ጉዳያችንን ለህብረቱ አቀርበናልን። ሞልታ በጣም ትንሽ ሀገር ስትሆን ንዑስ የስራ ገበያ ነው ያላት። ስለዚህ ጫና በዝቶባታል። እና ሞልታን በተመለከተ ተገን ጠያቂዎቹን በሌላ ቦታ በማስፈሩ ረገድ የህብረቱ ትብብር ያስፈልጋል ። »
ሞልታ EUREMA በሚል የተዘጋጀው አዲስ የመልሶ ሰፈራ መርሀግብር ተጠቃሚ ሆናለች። እአአ ከ 2005 ዓም ወዲህ በሞልታ ካሉት ስደተኞች መካከል ወደ 230 የሚጠጉ ተገን ጠያቂዎች ወደሌሎች የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች፡ ወደ 1,000 የሚጠጉ ደግሞ ወደ ዩኤስ አሜሪካ እንዲሄዱ ተደርጓል።
27 የህብረቱ አባል ሀገራት እስከ 2012 ዓምመጨረሻ ሊያወጡት ያሰቡት አንድ የጋራ የተገን አሰጣጥ ፖሊሲ የተገን ጠያቂዎቹ ሁኔታን ሊያሻሽል የሚችል ደንብ ያስተዋውቃል በሚል ተስፋ እንደተጣለበት በሞልታ የዩኤን ኤችሲአር ባልደረባ ፋብሪሲዮ ኤሉል ገልጸዋል።
«አንዳንድ ጥሩ የሚባሉ ማዕከላት አሉ። ሌሎች ልትኖርባቸው የማትችልም አሉ። አንድ በፍፁም የማንስማማበት ጉዳይ ግን ተገን ጠያቂዎቹ እንደ እስረኛ የሚያዙበትን ፖሊሲ ነው። በመሠረቱ፡ ተገን ጠያቂዎቹ መታሰር የለባቸውም ብለን ነው የምናስበው። »
ሎረንስ ሴረለስ /አርያም ተክሌ

Karte Malta - EU-Erweiterungsland
Karte Malta - EU-Erweiterungsland
Titel: Asylbewerber in Malta Asylbewerber in Malta 20/06/2012. Der Innenhof vom Safi Barracks 20/06/2012. Die Rechte gehören Laurens Cerulus, einem Korrespondenten der DW. Er hat uns die Rechte gegeben, seine Bilder auf dw.de zu veröffentlichen.
Asylbewerber in Maltaምስል Laurens Cerulus

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ