የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የጀርመን ኤንባሲ የአዉሮጳ ኅብረት ልዑካን እንዲሁም አምስት ምዕራባዉያን ኤንባሲዮች ከኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፊደሬሽን ጋር በመተባበር የ 2016 የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻንፕዮና ግጥሚያ ቅድሜ ሰኔ 4 ቀን አዲስ አበባ ላይ አዘጋጅተዋል። ከሰኔ 3 እስከ ሐምሌ 3 ቀን ድረስ የሚዘልቀዉና ፈረንሳይ ዉስጥ የሚካሄደዉ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻንፕዮና ነፀ-ብራቅ ነዉ በሚል በአዲስ አበባ ስቴዲየም ለአንድ ቀን በተካሄደዉ የእግር ኳስ ግጥምያ የተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራትን ወክለዉ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ታዳጊ ሕጻናት ተጫዉተዋል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

አዲስ አበባ በሚገኘዉ ስቴዲዮም በተዘጋጀዉ የእግር ኳስ ጨዋታ የተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራትንና አዉስትራልያን ወክለዉ የተጋጠሙት ወጣት የእግር ኳስ ቡድኖች የተዉጣጡት በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሲሆን የተመረጡትም በኤንባሲዎቹ ነበር።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ ስቴድዮም በነበረዉ የእግር ኳስ ግጥምያ ከ200 በላይ ተጫዋቾች የተሳተፉበት ሲሆን የጨዋታዉ ተመልካቾች በዕለቱ ዝግጅት መደሰታቸዉ ተመልክቶአል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

የ2016 የአዉሮጳ ሻንፕዮና ነፀ-ብራቅ ነዉ በተባለለት እና በአዲስ አበባ ስቴድየም በተካሄደዉ የእግር ኳስ ግጥምያ ላይ የተሳረፉት 15 ዓመትና ከዚያ በታች ዕድሜ ክልል የሚገኙ ታዳጊ ሕጻናት ነበሩ።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

ጀርመንን ወክለዉ በግጥምያዉ የተሳተፉት አዲስ አበባ ከሚገኘዉ የጀርመን ትምህርት ቤት የተዉጣጡ ተማሪዎች ሲሆኑ የተጋጠሙትም ከኔዘርላንድ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ነዉ።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

የፈረንሳይን ቡድን ወክለዉ የተጋጠሙት ወጣቶች የተዉጣጡት አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ከሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት ነበር።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ በተዘጋጀዉ የዘንድሮ የአዉሮጳ ሻንፕዮና ግጥምያ ላይ የተሳተፉት ወጣቶች ሰባት የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራትን ወከሉ ሲሆን በእንግድነት አዉስትራልያም ተሳታፊ ነበረች። አዉስትራልያን ወክለዉ የተጋጠሙት ከቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት የተዉጣጡ ታዳጊ ወጣቶች ነበሩ። በግጥምያዉ የአዉስትራልያ ቡድንን የወከሉት የቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዉድድሩን በአራተኛነት አጠናቀዋል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

አዲስ አበባ የሚገኘዉ የጀርመን ኤንባሲ ከዲፕሎማሲ ሥራዉ ባሻገር ከኅብረተሰቡ ጋር በቅርበት ለመገናኘት በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀትና እንዲሁም በዝግጅቱ በመካፈል ይታወቃል። ዘንድሮ የተዘጋጀዉ የአዉሮጳ እግር ኳስ ሻንፕዮና ነፀ-ብራቅ የእግር ኳስ ጨዋታም ከዚህ ዓላማ አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

ባለፈዉ ዓመት ሁለቱ ጀርመኖች የተዋሃዱበት ቀን ሲያከብሩ አዲስ አበባ የሚገኘዉ ኤንባሲ ባዘጋጀዉ መድረክ ወደ ሦስት ሺህ የሚሆኑ ወጣቶችና ሕጻናት ተካፋይ ነበሩ።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

አየርላንድን በመወከል የተጫወቱት ታዳጊ ሕጻናት የፍቅርና ሰላም ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸዉ። በግጥምያዉ ቡድን A ኔዘርላንድን ወክለዉ ያሸነፉት የሳሕለ ሥላሴ ቡድን ተጋጣሚዎች ሲሆኑ፤ ፈረንሳይን የወከሉት የሊሴ ገብረማርያም ት/ቤት ተማሪዎች በግጥምያዉ በሁለተኛ ደረጃነት ነዉ ያጠናቀቁት።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

በግጥምያዉ በእንግድነት የተሰሳተፈዉ የአዉስትራልያ ቡድንን የወከሉት የቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዉድድሩን በአራተኛነት አጠናቀዋል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

ጀርመንን የወከሉት የጀርመን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ዉድድሩን በሦስተኛነት ነዉ ያጠናቀቁት። በቡድን B የተሰለፉት ከተለያዩ ትምህርት ቤት የተዉጣጡ ተጋጣሚዎች ለአየርላንድ ቡድን የተሰለፉ ነበሩ። ኢጣልያን ወክለዉ የተጫወቱት የኢጣልያ ትምህርት ቤት ተጋጣሚዎች ናቸዉ። ቼክ ሪፐብሊክን ፤ የአዲስ ዘመን ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ለዴንማርክ የጀርመን ቤተ-ክርስትያን ትምህርት ቤት ተማሪዎች በግጥሚያዉ ተሳትፈዋል። ለግማሽ ፍጻሜ ኔዘርላንድ ከኢጣልያ፤ አየርላንድ ከፈረንሳይ ተጋጥመዉ፤ ፈረንሳይና ኔዘርላንድ ከየምድቡ አሸንፈዉ ለዋንጫ ግጥምያ ደርሰዋል።

የ2016 የአዉሮጳ ሻምፕዮና ነፀብራቅ በኢትዮጵያ

የአዉሮጳ እግር ኳስ ግጥምያ በአዲስ አበባ

ለዋንጫ ግጥምያ የደረሱት የነዚህ ሁለቱ ሃገራት ተጋጣሚዎች ከፍተኛ ጨዋታን አሳይተዉ ኔዘርላንድ ፈረንሳይን ሁለት ለባዶ በመርታት የዋንጫዉ ባለቤት ሆናለች። በአዲስ አበባ ስቴድየም ለአንድ ቀን የተካሄደዉ የ2016 የአዉሮጳ እግር ኳስ ሻንፕዮና ጨዋታ ነፀ-ብራቅ ግጥምያ ጠንካራ ፉክክር የታየበት ነበር። ምርጥ የሴት እግር ኳስ ተጫዋች ከኔዘርላንድ፤ የወንድ ጠንካራ ተጫዋች ደግሞ ፈረንሳይን ወክለዉ ከተጫወቱ ወጣቶች ተመርጠዋል። በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ለኔዘርላንድ የተጫወተዉ ወጣት፤ ምርጥ በረኛ ደግሞ ኢጣልያን ወክሎ በግጥምያዉ ላይ የተሳተፈ ወጣት በመሆን ተመርጧል።

አውዲዮ ናው 24/7 - በየቀኑ የሚተላለፈውን የዶይቸ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ለማዳመጥ በቀጣዮቹ የአውዲዮ ናው ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ።

ዝግጅቶቻችን በድምፅ

የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ 16:00 - 17:00

የአንድ ሣምንቱ የስርጭት ኮሮጆም "ዝግጅት"ን በመጫን ሊገኝ ይችላል። የአማርኛ፣ የኪስዋሂሊ፣ የሀውሳ፣የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሣይኛ እና የፖርቱጊዝኛ ቋንቋ ሥርጭት በሚተላለፍበት ጊዜ በኢንተርኔት በInternet Explorer 8 በቀጥታ ማድመጥም ይቻላል። በፌስቡክ፣ በዋትስአፕ እና በviber public chat DW Amharicም ልታገኙን ትችላላችሁ። አስተያየታችሁ ዓቢይ ግምት የሚሰጠው ነው፤ በ +49-228-429-164995 ደውሉልን። በዕለቱ ዓቢይ ርዕስ ላይ በ+49 -162-1056831 በSMS አስተያየት ላኩልን። ባጠቃላይ በዝግጅታችን ላይ አስተያየታችሁን በኢሜይልም ልትልኩልን ትችላላችሁ።

amharic@dw.com

የስርጭት እና የሞገድ መሥመሮች

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

ጠንካሮቹ ዝሆኖች

የጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም አፍሪቃ እግር ኳስ ግጥምያ አሸናፊዎች የዘንድሮን ዋንጫ ይወስዳሉ ተብሎ ከሚገመቱት ቡድኖች መካከል ቀዳሚዉን ስፍራ ይዘዉ ይገኛሉ። ምንም እንኳ የ «ወርቃማዉ» ትዉልድ ተጫዋቾች ዲደየር ድሮግባና ያያ ቱሬ ቡድኑን ለቀዉ ቢወጡም፤ የኮት ዲቯር አሰልጣኝ ሚሻኤል ዱሱየር በቡድኑ ምርጥ የሚሏቸዉን አንድ ሁለት ብለዉ መቁጠር ይችላሉ። የኮት ዲቯሮቹ ዝሆኖች ሁሉም ማለት ይቻላል እንደስያሜያቸዉ ሁሉ ዳጎስ ያለዉን ደሞዛቸዉን የሚያገኙት በአዉሮጳ ቡድኖች ዉስጥ በአጥቂነት ተሰልፈዉ በመጫወት ነዉ። ለምሳሌ ዊልፍሬድ ቦኒ«ቀኝ»፤ ዊልፍሪድ ዛሃ ፤ ኤሪክ ባጂን መጥቀስ ይቻላል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

የመጀመርያዉ የድል ሕልም

በፊፋ የዓለም ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋች ቡድን መዘርዝር 33ኛ ላይ የሚገኘዉ የሴኔጋሉ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ወቅት ጠንካራና ምርጥ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ቡድን ነዉ። ሳዲዮ ማኔ «ግራ» በእንግሊዙ ፕሪሜር ሊግ ከሊቨርፑል ጋር ዉል ተፈራርሞአል። የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ባልደረቦቹ በበኩላቸዉ በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ ላይ ለአገሩ ተሰልፎ በአሸናፊነት ዋንጫዉን ወደሃገራቸዉ ማስገባት ይፈልጋሉ። ሴኔጋል እስካሁን ከተካሄዱት የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያዎች መካከል በጎርጎሮሳዉያኑ 2002 ዓ.ም በሁለተኛነት በማጠናቀቅ ጥሩ ዉጤት አስመዝግባለች።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

ክንፋሙ ግሥላ

የጋቦን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ደጋፊዎቻችን ክንፍ ሊያዉሱን ይችላሉ የሚል ተስፋን ሰንቀዋል። ግሥሎቹ ከስከዛሬዉ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያ ከሩብ ፍጻሜ አልፈዉ አያዉቁም። የጋቦን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በተለይ በብሔራዊ ቡድኑ አጥቂ በፒየር ኤሜሪክ አዉባሜያንግ «ግራ» ላይ ተስፋቸዉን ጥለዋል። ፒየር በጀርመኑ «ቡንደስሊጋ» ለቦርስያ ዶትርሙንድ ተሰልፎ 16 ግቦችን በማስቆጠር በድንቅ አጥቂ ተጫዋች መዘርዝር ዉስጥ ተመዝግቧል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

ዳግም ለማሸነፍ ማሪዝን መያዝ ?

በጎርጎረሳዉያኑ 2014 ዓ.ም የተካሄደዉ የዓለም የእግር ኳስ ጨዋታ ትዝታ የሚጠፋ አይደለም። ብራዚል ላይ በተካሄደዉ በዚህ ግጥምያ ሩብ ፍጻሜ የደረሰዉ የአልጀርያዉ ቡድን፤ በግጥምያዉ ቆየት ብሎ ዋንጫዉን እጁ ያስገባዉን የጀርመንን ቡድን ማንገዳገዱ ይታወሳል። በበረሃማዋ አልጀርያ ያደገዉ የቡድኑ አጥቂ ሪያድ ማህሬዝ «ግራ» በቅርቡ የአፍሪቃ የዓመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በመባል መሸለሙ ይታወቃል። አልጀርያ ለመጀመርያ ጊዜ በጎርጎረሳዉያኑ 1990 ዓ.ም የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያን ማሸነፏ ይታወሳል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

ጥቋቁሮቹ ኮከቦች ከሁለተኛነት ከፍ ማለትን ይሻሉ

ጥቋቁሮቹ ኮከቦች ደረጃን ጠብቆ ለማለፍ እንደ ባህላቸዉ ታዋቂዉን አጥቂ አንድሪ አየዉን ማስገባታቸዉ የተለመደ ነዉ። አንድሪ አየዉ ሦስት ግዜ የአፍሪቃ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሞአል። የጋና ብሔራዊ ቡድንም የአህጉሪቱን የእግር ኳስ ግጥሚያ ሦስት ጊዜ አሸንፎአል። ቢሆንም ቡድኑ የመጨረሻዉን የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ ያሸነፈዉ የዛሬ 35 ዓመት ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም በተካሄደዉ የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያ ጋና ለመጀመርያ ጊዜ ለዋንጫ ቀርባ በፍጹም ቅጣት በኮት ዲቯር መሸነፍዋ ይታወቃል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

የፈርኦኖቹ መመለስ

በማሸናፍ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የአፍሪቃዉ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዉድድር ሜዳዉ ዳግም ተመልሶአል። በአፍሪቃ አህጉር የዋንጫ ግጥምያ ላይ ለመሳተፍ የማጣርያ ግጥምያን ሦስት ጊዜ ማለፍ ያልቻለዉ የግብፅ ቡድን ሰባት ጊዜ ዋንጫን በጁ ያስገባ ጠንካራ ቡድን ነዉ። ግብፅ ዘንድሮ በጋቦን የሚካሄደዉን ግጥምያ ለመሳተፍ ማጣርያዉን አልፋ ቀርባለች ሞሃመድ ሳላህን «ቀኝ 2ኛ» ጨምሮ ሌሎች ፈርኦኖች ልክ እንደ ጎርጎረሳዉያኑ 2010 ድል ሁሉ ዋንጫዉን ይዘዉ ይመለሳሉ የሚል ጠንካራ እምነት አለ።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ዋንጫ፤ ያሸንፋሉ ተብለዉ የሚጠበቁ ቡድኖች

የስኬታማነት ስልት ለስኬታማ አሰልጣኝነት?

እንደ እቅዱ ቢሆን ኖሮ የጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ,ም የአፍሪቃ ዋንጫ ግጥምያ የሚካሄደዉ በሞሮኮ ነበር። ተነሳ የተባለዉን የኤቦላ ወረርሽኝ ተከትሎ ሞሮኮ፤ ጨዋታዉን ማስተናገድ ባለመፈለግዋ ግጥምያዉ በኢኳቶሪያል ጊኒ ተካሂዶአል። የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ግን በጫወታዉ እንዳይሳተፍ ታግዶ ነበር። ዘንድሮ ግን አዚዝ ቦሃዱዝ «ግራ» እና ባልደረቦቹ ጋቦን በሚካሄደዉ ግጥምያ ሜዳ የኳስ ጨዋታ ማለት እንዴት እንደሆነ ማሳየት ይፈልጋሉ። አሰልጣኝ ሃርቨ ሬንአርድ በዚህ አይታሙም፤ ምክንያቱም በጎርጎረሳዊዉ 2012 ዓ.ም የዛምቢያ አሰልጣኝ ነበሩ፤ በ2015 ደግሞ ኮት ዲቯርን ለዋንጫ አብቅቷል።

አውሮጳ፣ የስደተኞች ሕልም

ተከታተሉን

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو