አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:18 ደቂቃ
ባህል | 26.05.2019

ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከDW ጋር

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«ከተማችን ላይ ዘመናዊነት እየታየ ነዉ፤ ዘመናዊነት ግን ሥነ-ዉበትን አካቶ መሆን አለበት የሚልም እምነት ስላለን በቀለም ቡሩሻችን ለዓይን የሚታክተዉን ለአዕምሮ የሚያዳግተዉን ድንጋያ በጥበብ ለመሸፈን ሞክረናል፤ ሥዕሎቻችን ጥበብ በጎዳና የሚል መልክትንም ይዘዋል» የኢትዮጵያ ሠዓልያን ማኅበር

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

አዲስ አበባችን ድንጋያማ ገፅታ ከሚኖራት «ዲዛይኖቹን በኢትዮጵያ ባህላዊ እቃዎች አምሳል የተለያዩ ታሪካዊና ተፈጥሮዋዊ ነገሮችን በመሳል ነዉ ድንጋያማዉን ገፅታ ለመሸፈን የሞከርነዉ። በሌላ በኩል ከተማም ስለሆነ አረንጓዴ ነገር ያስፈልገዋል በሚል፤ አደይ አበባን ዲዛይን አድርገን ሠራን።» ይላሉ ፤ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሥነ-ጥበብ ባለሞያዎች!

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

« እንደሚታወቀዉ አዲስ አበባ የተለያዩ መንገዶች ተሰርታዉላታል። መንገዱ ተሰርተዉ ካለቁ በኋላ መንገዱ ላይ በርካታ ሰፋፊ ኮንክሪቶች ሆኖ ተከቦ ታየ። እነዚህ ሰፋፊ ድንጋዮች ለተመልካች አንዳንዴ መንገዱ ተሰርቶ ያላለቀ ስሜትን ሁሉ ይፈጥራሉ። እና እዚህ ላይ ሥዕል ብንስልበት እያልን እንጓጓ ስለነበርን ህልማችን እዉን ሆንዋል።»

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«አዲስ አበባ ከተማችን የአፍሪቃ መዲና ናት፤ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫም እየሆነች ነዉ። ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መቀመጫም ናት። በዚህም ቀለሞችዋ እየበዙ ነዉ የሚል እምነት አለን። እነዚህ ቀለማት ደግሞ አዲስ አበባን የሚወክሉ የአደይ አበባ ማለትም አዲስ የሚመጣ አበባ፤ በሚል የተወሰኑ ሥራዎችን ሰርተናል» የኢትዮጵያ ሠዓልያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ስዩም አያሌዉ

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

የኢትዮጵያዉያን የማበጠርያ አይነቶችንም በጎዳናw ስዕሎቹላይ ለማሳየት ተሞክሮአል። እነዚህ ማበጠርያ አይነቶች ከዘጠኙም ክልሎች የመጡ ናቸዉ፤ የአፋር ፣ የትግራይ፤ የሃረር፤ የጎንደር የደቡብ አካባባ ማበጠርያዎች ሁሉ ናቸዉ የተሳሉት። ሰዉ እነዚህን ማበጠርያዎች ሲያይ ምንድነዉ ከየትነዉ ሲል ይጠይቃል፤ በሌላ በኩል ሃገሪቱንም ይተዋወቃል። በአዲስ አበባ ከተማ የዉበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማትና አስተዳደር ተቋም ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

ጥበባዊ ሥራዎች ወደ ጎዳና ሲወጡ ኅብረተሰቡ ሥለ-ጥበብ የተሻለ ግንዛቤ ይኖረዋል፤ ከዚያም አልፎ ለከተማዋ ዉበት ሌላ ገፅታ ነዉ።

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«አዲስ አበባ ጎዳና ላይ ከሚታዩት ስዕሎች መካከል፤ ከጥንታዊ ዘመን የዋሻ ስዕሎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ማለት እስከ 18ኛ ክፍለ ዘመን ድረስ ያሉ ቅርሶችን ነዉ ለማሳየት የሞከርነዉ። ላሊበላ፤ አክሱም፤ በአልባሳት ላይ ያሉ ጌጣጌጦች፤ ጥለትን የመሳሰሉት ለየት ያሉ ስለሆኑ ትልቅ ዉበት ናቸዉ። በቀጣይ የኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ብቻ ብለን ልንሰራቸዉ ያሳብናቸዉ ትልቅ ነገሮችም አሉ። » የኢትዮጵያ ሠዓልያን ማኅበር

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«ጎዳናዎች ላይ የቆሙት የኮንክሪት ድንጋዮች በቀለማት በተለይም ደግሞ ባህላዊ ምስሎችን በሚያንፀባርቁ ምስሎች በአማርኛ ፊደላት በግዕዝ ቁጥሮች በአበሻ ልብስ የጥበብ ዲዛይን ሁሉ መሞላታቸዉና በጎዳናዉ ለሚዘዋወረዉ ሕዝብ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረለት ነዉ የተነገረዉ።» የሠዓሊያንና የቀራፂያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሠዓሊ ሰይፉ አበበ

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«የከተማ ዉበት በሕንጻ ፤ በአካባቢ አጥሮች ፤ በቀለም የሚገለጽ ነዉ የሚሆነዉ። ሁለተኛ ዉበት በጣም የብዙ ነገሮች ድብልቅ ነዉ። በዉስጡ ባህል፤ ታሪክ፤ አኗኗርን ሁሉ አካቶአል። ዉበት ማንነትን ገላጭ ነዉ። ሃገራችን ቁጥር ስፍር የሌላቸዉ ማንነታችንን ከፍ የሚያደርጉ ባህላዊ እሴቶች አሏት። ስለዚህ እነዚህን የመንገድ አካፋዮች ለዓይን ጥሩ ገጽታ እንዲኖራቸዉ ማድረግ አለብን፤ ብለን ተነሳን።» የአዲስ አበባ የዉበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፍያ ልማትና አስተዳደር ተቋም

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

ስዕሎችን ለመሳል የተጠቀምነዉ የብረት ቀለም ነዉ። ይህ ቀለም ጥሩ ወዝም እንዳለዉ እናዉቃለን። ሰዓሊ ስለሆንም ምን ቀለም መጠቀም እንዳለብን። የትኛዉ ነዉ ጥሩ ቀለም ብለን እንመርጣለን። በሚቀጥለዉ ጊዜ ግን ከአንዳንድ የቀለም ፋብሪካዎች የተሻለ ቀለም የሚባለዉን ፤ አስር አስራ አምስት ዓመት መቆየት የሚችለዉን ቀለም ለመጠቀም እንሞክራለን። እስካሁን ግን ጎርፍም ሆነ ዝናብ ያበላሸዉ ወይም ያጠዉ ስዕል የለም። እንደዉም ዝናቡ የመኪና ጢስ ምናምን ያጠቆረዉን ስዕል አጠበዉ።

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

«በቀጣይ የሃረር ግንብ የአክሱም ሃዉልቶች ፤ የላሊበላ ዉቅር ቤተክርስትያናት፤ የጥያ ትክል ድንጋዮች ፤ በባሌ የሚገኘዉ ዋሻ አለ፤ ፋሲለደስ የመሳሰሉ ኢትዮጵያን የሚገልፁ በርካታ ታሪካዊ ቦታዎችም አሉን። ከዚህ በተጨማሪ የኛን ማንነት የሚገልጹ አለባበሶች የፀጉር ሥራዎች፤ የአመጋገብ ሥርዓቶች ሁሉ አሉን። እነዚህን ነገሮች ራሳችን መግለፅ በምንችልበት ሁኔታ ቀለማትንም ጭምር በነዚህ ኮንክሪቶች ላይ እንዲያርፉ እንፈልጋለን።» የአዲስ አበባ የዉበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፍያ ልማትና አስተዳደር ተቋም

የጎዳና ሥነ-ጥበብ በአዲስ አበባ

የጎዳና ጥበብ

በአዲስ አበባ የዉበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፍያ ልማትና አስተዳደር ተቋም፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና የቀራፂያን ማኅበር ያለምንም ክፍያ ለከተማዋ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች ይህን ልዩ የጎዳና ላይ ጥበብ የሠሰሩ ሠዓልያን ከልብ አመስግነዋል።

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

የዓለማየሁ ተፈራ ስራዎች

ሠዓሊ፣ ዓለማየሁ ተፈራ

ተከታተሉን

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو