በአፍሪቃ በኢኮኖሚዉ እያደጉ ያሉት ሀገሮች እድገታቸዉ የተፋጠነዉ ጥሬ ሃብታቸዉን ለዓለም ገበያ በማቅረባቸዉ ነዉ። ከምያቀርቡት ጥሪ ሃብታቸዉ ዉስጥ፤ ለምሳሌ እንደ መዳብ እና ነሃስ እንዲሁም እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያላጠዉ ማዕድናት ማለት እንደ ወርቅ፣አልማዝ፣ ከመሪት ዉስጥ የሚገኝ ነዳጅ እንዲሁም ጋዝ የመሳሰሉት ይገኙበታል።

እንደ አንጎላ ያሉ አንዳንድ የነዳጅ ዘይት አምራች አገራት፣ የዓመት የእድገት መጠናቸዉን ከ20 በመቶ በላይ ሲያደርሱ፤ ሌሎች ሀገራት ደግሞ ማዕድንም ሆነ የነዳጅ ዘይትን ማዉጣት የጀመሩት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ነዉ። የፖርቱጋል ቋንቋ ተናጋሪዋ ሞዛንቢክ ለምሳሌ በዓለማችን በከፍተኛ ደረጃ ከሰልን እና ጋዝን ለማምረት ጥሩ ጅማሮ ላይ ናት። የዓለማችን ኢኮነሚ በጥሪ ሃብት እጥረት ሲጨናቅ- የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገቷ በመፋጠን ላይ ይገኛል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የአፍሪቃ ጥሪ ሃብት ምርት መጠናከር፤ በዓለም የገበያ ዋጋ ላይ እና በአቅርቦት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ፤ የአህጉሪቱ ኢኮነሚ ላይ ተፅኖ ሊያሳድር ይችላል። በሌላ በኩል ጥሪ ሃብቱን በማከፋፈሉ ረገድ የከባቢ አየር መበከል፣ ሙስና እና ግጭቶች አዲስ በተጠናከረዉ ምጣኔ ሃብት ላይ ጉዳትን ያስከትላሉ። "በቂ የጥሪ ሃብት" በከርሰ ምድራቸዉ መገኘቱ እድገትን ሊያስገኝላቸዉ ሲገባ፤ ችግርን ይዞባቸዉ መጥቶ ይሆን? ይዚህ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለ ኢኮነሚ፤ ለአፍሪቃ ሀገራት እና ህዝቦችዋ የሚያመጣላቸዉ ጥቅም ምን ይሆን? የዶቼ ቬለ ዘጋቢዎች መልስ ያፈላልጋሉ።

ተከታተሉን

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو