1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብርሀን የባህል ማዕከል 

ረቡዕ፣ ሐምሌ 12 2009

የአዲስ አበባን መንገድና አዉራ ጎዳናዎች ለማዘመን በተያዘው እቅድ መሠረት በቅርቡ ይፈርሳሉ ከሚባሉ የመኖሪያ ቤትና ሕንጻዎች መካከል ብርሃን ኢትዮጵያ የባህል ማዕከል አንዱ መሆኑን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሳቢያ በላይነሽ ዓባይ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2goT9
Äthiopien Kulturcenter in Addis Abeba
ምስል DW/Getachew Tedla

Ber. AA(Berhan Ethiopia Cultual Center risks demolition) - MP3-Stereo

ወይዘሮ በላይነሽ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስረዱት፣ በማዕከሉ አጥር ላይ በየጊዜው ተለጥፈው ያዩዋቸው ጽሁፎች፣ ማዕከሉ የቆመበት ቦታ «የአዲስ አበባን መንገድ ለማልማት የተያዘዉን እቅድ ተግባራዊነት ያሰናክላል የሚል መልዕክት ይዘዋል»። ከ30 ዓመታት በፊት የተቋቋመው ይህ  ማዕከል የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ባህል በአንድ ስፍራ አሰባስቦ ለእይታ ያቀረበ ነው። የአዲስ አበባ ወኪላችን የማዕከሉን ሥራ አስኪያጅና  እና  የኢትዮጵያ የባህል ሚኒስቴር አማካሪና የሃገርና የዓለም አቀፍ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ