1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደማስቆ፤ የአረብ ሊግ ታዛቢዎች ዉሎ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2004

ሶርያ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለመመልከት የተላኩት የአረብ ሊግ ታዛቢዎች ዛሬ ሆምስ የተባለችዉን ከተማ መጎብኘታቸዉን ሮይተርስ ዘገበ።

https://p.dw.com/p/13aMe
ታዛቢዉ ቡድንምስል picture-alliance/dpa

የመብት ተሟጋቾች ትናንት እዚች ከተማ 34ሰዎች በመንግስት ኃይሎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉን አመልክተዋል። ዛሬ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ባይገለፅም ታዛቢዎቹ በተገኙበትም ከ20ሺ የሚበልቁ ወገኖች ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉም ተገልጿል። በፕሬዝደንት ባሽር አልአሰድ አስተዳደር ላይ ተቃዉሞ ከተጠናከረባቸዉ ግዛቶች በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀሰዉ የሆምስ ከተማ ኗሪ የሆኑት እኝህ ሴት የጸጥታ አስከባሪዎችን ይፈፅሙታል ያሉትን ሲገልፁ፤
«በአንድ አካባቢ ተቃዉሞ የተካሄድ እንደሆነ ሁሉንም ይቀጣሉ፤ የታንክ አረር ይተኩሳሉ፤ የምግብ፤ የነዳጅም ሆነ የጋዝ አቅርቦትን ያቋርጣሉ።»
እንዲያም ሆኖ ዛሬ የአረብሊግ ታዛቢዎች ወደከተማዋ ሲገቡ የመንግስት ታንኮችና ወታደሮች ሲወጡ ታይተዋል። የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸዉ ትናንት በተጠቀሰችዉ ከተማ ጥይት ሲያዘንቡ ከነበሩት ታንኮች ጥቂቱ እዚያዉ ሳይደበቁ እንዳልቀረ ያሳስባሉ። የአረቡ ሊግ የላካቸዉ ታዛቢዎች በዋነኛነት የፕሬዝደንት አልአሰድ መንግስት ቃሉን መጠበቁን ይመለከታሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ