1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደራሲ ሮማን ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር ማን ናት?

ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2014

«እናቴ እንጊሊዛዊት ናት። ኢትዮጵያ ዉስጥ የክብር ዜግነት ተሰጥቶአት፤ ከሃምሳ ዓመት በላይ ኖራለች። ስትሞትም የተቀበረችዉ እዚሁ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ክርስታና ተነስታለች። እናቴ በጣም ኢትዮጵያዊ ነበረች። ወደ ሥነጽሑፉ እንዳዘነብል ብዙ ሚናን ተቻዉታለች። ሙዚቃን አስተምራናለች።»

https://p.dw.com/p/437pn
Äthiopien Autorin Roman Tewolde-Berhan
ምስል Privat

እናቴ ወደ ሥነ-ጽሑፍ እንዳዘነብል ትልቅ ሚናን ተጫዉታለች

«እናቴ እንጊሊዛዊት ናት። ኢትዮጵያ ዉስጥ የክብር ዜግነት ተሰጥቶአት፤ ከሃምሳ ዓመት በላይ ኖራለች። ስትሞትም የተቀበረችዉ እዚሁ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ክርስታና ተነስታለች። እናቴ በጣም ኢትዮጵያዊ ነበረች።»

Äthiopien Autorin Roman Tewolde-Berhan | Buch Reflections

በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነችዉ ደራሲ የንግድ አስተዳደር ባለሞያዋ፤ ሮማን ተወልደ ብርሃን ገብረግዚአብሔር ትባላለች። በኢትዮጵያ በሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ብዙ ስራን እየሰራች ነዉ። ከ 50 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያን አኗኗር እና ባህል ባህል ተቀብለዉ የኖሩት የአካባቢ ተፈጥሮ  ተቆርቋሪ፤  የሀገር በቀል እዉቀቶች አድናቂ የነበሩት እናትዋ ሱ ኤድዋርድስ፤ ወደ ሥነ-ጽሑፉ እንድታዘነብል ከፍተኛ አስተዋጽዎ ማድረጋቸዉን ሮማን ትናገራለች። የመጀመርያ ዲግሪዋን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፤ በእንጊሊዝ ሃገር ደግሞ በየሂሳብ እና በንግድ አስተዳደር ሞያ የማስትሪት ዲግሪዋን አግንታለች። ሮማን ተወልደ ብርሃን ገብረግዚአብሔር፤ ኑሮዋን በእንጊሊዝ ሃገር እንድርጋም ነበር።  ሮማንን ፤ ሮማን ተወልደ ብርሃን ገብረግዚአብሔር ማን ናት ስንል ነበር በቅድምያ ጥያቄን ያቀረብንላት።

«ሮማን ተወልደብርሃን ፤ መጽሐፍ ትፅፋለች፤ መጽሐፍ  ማሳተም እና ማከፋፈል ሥራዬ ነዉ። ከዚህ በፊት ለአንባብያን በእንጊሊዘኛ« ሪፍሊክሽን » የተባለ  አንድ የግጥም መድብል አሳትሜያለሁ። ለታዳጊ ወጣቶች የሚሆን በአማረኛ አንድ ልቦለድ ጽፌያለሁ። በአብዛኛዉ ሥነ-ጽሑፍ ነገሮች ላይ ነዉ የምሰራዉ። በዚህ ሞያ እንድሰራ ቤተሰቦቼ ትልቅ ተጽእኖ አድርገዉብኛል። ሴት ጻሕፍትን ማበረታታት በጣም ደስ ይለኛል። በቅርብ የጀመርኩት ሮማናት የሚል መጽሐፍ አሳታሚ እና አከፋፋይ ድርጅት አለኝ። ከዚህ በፊት በእርግጥ በተለያዩ ሞያዎች አገልግያለሁ። እንጊሊዝ ሃገር ለተወሰኑ ዓመታት ኖርያለሁ። አሁን ግን ኑሮዬን ያደረኩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። አባቴ ተወልደ ብርሃን ገብርግዚአብሄር ይባላል። የምኖረዉ ከአባቴ ጋር ነዉ። 84 ዓመት ሞልቶታል። እናቴ የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። እናቴ ወደ ሥነ-ጽሑፍ ዘርፉ እንድሳብ ትልቅ ሚናን ተጫዉታለች። ከልጅነቴ ጀምሮ መጽሐፍ ታነብልኝ ነበር።  ሙዚቃንም አስተምራኝለች።»  

[No title]
ምስል Privat

እንጊሊዝ ሃገር ኑሮዉ እንዴት ነበር ? አሁንስ ወደ ሃገር ቤት ጠቅልለሽ ስትገቢ ፤ ሁኔታዉ አልከበደሽም?

« በእርግጥ ትልቅ ተግዳሮት ነበረዉ። ከኢትዮጵያ ወጥቼ ወደ እንግሊዝ ሃገር ስሄድ ወጣት ነበርኩ ። አዲስ አበባ ያኔ የነበራት ስፋት፤ ያኔ የነበረዉ የሕዝብ ብዛት አሁን የለም። አዲስ አበባ እጅግ ሰፍታለች። በጣም ብዙ ህዝብ ነዉ ያለዉ። ትራንስፖርቱም ቢሆን አሁን  ቀላል አይደለም። ያኔ ትራንስፖርት ማግኘት ቀላል ነበር። ፤ ማኅበራዊ ኑሮዉ በፊት ቀላል ነበር። ከጓደኛ ጋር መገናኘት ይቻል ነበር። አሁን ግን ሁሉም በየፊናዉ የሚሮጥ ነዉ። አልያም በየኮንደሚኔሙ ዘግቶ ብቻዉን ነዉ የሚኖረዉ። በአጠቃላይ ከእንጊሊዝ ሃገር ጠቅልዬ ስመለስ አዲስ አበባ ያኔ ጥያት ስሄድ የነበራት ቁመና ላይ ያሆና አላገኘኋትም። ሁሉ ነገር ቀላል አይደለም። በተለይ የትራንስፖርት የመጓጓዣ ችግር አለብኝ»  

ስንት ጊዜ ሆነሽ ወደ ኢትዮጵያ ጨርሰሽ ከተመለሽ? እንጊሊዝ ስንት ጊዜ ቆየሽ?  ለንደን ነበር የምትኖሪዉ ?

Äthiopien Autorin Roman Tewolde-Berhan
ምስል Privat

« የምረዉ ለንደን ከተማ ነበር። እንጊሊዝ ሃገር  ወደ አስር ዓመት ኖሬያለሁ። ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ ሰባት ዓመት ሆነኝ»

ሮማን እንጊሊዝ ሃገር ኖረሽ አሁን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰሽ በተለይ ደሞ በህትመቱ ረገድ ብዙ መጽሐፍን አሳትማለች፤ መጽሐፍትንም ታከፋፍላለች።  በቅርቡ   ከ 13 ፀሐፍት ጋር በጋራ  ጉራማይሌ የተባለ የግጥም መድብልን ለአንባቢያን አብቅታለች። 

ሮማን ተወለደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር፤ በእፅዋት ብዘሃ ህይወት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስራን የሰሩ ኢትዮጵያዊ ጠበብት የዶ/ር ተወለደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር ልጅ ናት። ሮማን አጎትዋ ደራሲ ስብሃት ገብረግዚአብሄር ለሥነ-ፅሑፍ ስራዎችዋ ማበብ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግራለችም። ሮማን ተወለደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር በቃለ ምልልሱ መጨረሻ  ለሃገራቸዉ መስራት የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን የግድ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ወይም መመለስ አያስፈልጋቸዉም፤ ነገር ግን ጠንክሮ በመጣር ያለሙበት መድረስ ይቻላል፤ የማይቻል ነገር የለም። ጊዜዉ ቴክኖሎጂ የሰፋበት በመሆኑ ሃገርንም በቅርበት ሆኖ መርዳት ወገንን መደገፍ ይቻላል ስትል ሰፋ ያለ መልክት አስተላልፋለች። ከሮማን ተወልደ ብርሃን ገብረግዚአብሔር ጋር ያደረግነዉን ሙሉ ቃለ-ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመቻን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

Äthiopien Autorin Roman Tewolde-Berhan
ምስል Privat

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ