1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳናና የአፍሪቃ ሕብረት

ዓርብ፣ የካቲት 28 2006

የጎሳ ልዩነት መልክና ባሕሪ በያዘዉ በደቡብ ሱዳኑ ጦርነት በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።ከዘጠኝ’ መቶ ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ ደግሞ አንድም ተሰዷል፥ አለያም ተፈናቅሏል።

https://p.dw.com/p/1BM0J
ምስል DW/G. Tedla


የአፍሪቃ ሕብረት በደቡብ ሱዳኑ ጦርነት በሠላማዊ ሠዎች ላይ የተፈፀመዉን በደል የሚመረምር ልዩ ኮሚሽን መሰየሙን አስታወቀ።የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ድላሚኒ ዙማ ዛሬ እንዳስታወቁት ኮሚሽኑ ዋና ፅሕፈት ቤቱን አዲስ አበባ አድርጎ በደቡብ ሱዳን ሕዝብ ላይ የደረሰዉን በደል የሚመረምሩ ባለሙያዎችን ያሰማራል።የጎሳ ልዩነት መልክና ባሕሪ በያዘዉ በደቡብ ሱዳኑ ጦርነት በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ሠላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ ተዘግቧል።ከዘጠኝ’ መቶ ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ ደግሞ አንድም ተሰዷል፥ አለያም ተፈናቅሏል።ጌታቸዉ ተድላ ኀይለ ጊዮርጊስ ዝር ዘገባ አለዉ

ጌታቸዉ ተድላ ኀይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ