1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳንና መልክአ-ምድሯ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 9 2005

ወደ 50 ዓመታት ያህል የጦር አውድማ ሆና የቆየችው ደቡብ ሱዳን ነጻ ከወጣች ገና ዓመት ከመፈንቅ ነው የሆናት። የፖለቲካ ካርታዋ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገባ ተለይቶ አይታወቅም። የተፈጥሮ ሀብቷም መጠን እንዲሁ! አሁን ግን ፤ የጁባ ዩንቨርስቲ ፤ በርሊን

https://p.dw.com/p/174zs

ከሚገኘው BEUTH ከፍተኛ የቴክኒክ ተቋም ጋር በመተባበር፤ የራሷን መልክአ-ምድራዊ ካርታ አቅድ ባለው ሁኔታ ለማሰናዳት ተዘጋጅታለች። ዩታ ሽቬንግስቢር ያሰናዳችውን ተክሌ የኋላ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

Südsudan Geoinformation Ressourcen Entwicklung Palouge Juba Vermessung
ምስል Jutta Schwengsbier

ትንንሾቹ የጭቃ ቤቶች ከጎናቸው በተሠራ ሰማያዊ ቀለም ባለው ረጅም ህንጻ ተውጠዋል። የቻይናና የማሌሺያ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች፤ በላዕላይ ነጨ ዐባይ ደፍድፍ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አውታሮች ተክለዋል፤ ቧንቧዎችንም ዘርግተዋል። ይሁንና የአካባቢው ህዝብ ገና የዚህ የተፈጥሮ ሀብት ትሩፋት ተቋዳሽ አልሆነም። ደቡብ ሱዳን ያላት የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት መጠን የአፈርና ቋጥኝ ተመራማሪ ጆሰፍ ሌጎ ጀምስ እንደሚሉት ገና አልታወቀም።

«ነጻ እንደወጣን፤ ማንኛውም መረጃ በሰሜን ሱዳናና ከዚያ ውጭ እንጂ፣ በእኛ እጅ አልነበረም። መረጃው ተነፍጎን ነበር።ለትምህርት ወደ ውጭ የሚሄድ ሰው፤ ብዙ መረጃ በዚያ እንደሚገኝ ይገነዘባል፤ ግን አያገኘውም። መግዛት ይኖርበታል። እኔ ራሴ አሁን እንደ ደቡብ ሱዳናዊ የአፈርና ቋጥኝ ባለሙያ ራሴ ነኝ ካርታውን በአዲስ መልክ ማዘጋጀት የሚኖርብኝ።»

Sudan Südsudan Addis Abeba Gipfel Treffen Salva Kiir
ምስል Reuters

ጆሰፍ ጄምስ፤ የደቡብ ሱዳንን የተፈጥሮ ሀብት በአቅድ በማጥናትና በማመላከት ረገድ ከቀደምት የአገሪቱ ጠበብት አንዱ ናቸው። የበርሊኑ BEUTH የሥነ ቴክኒክ ከፍተኛ ተቋም ሥልጠና ከሰጣቸው በኋላ እርሳቸውና ሌሎች የጁባ ዩንቨርስቲ ባልደረቦቻቸው አሁን በሥርዓት የመልክአ-ምድራዊ ሰነድ ለማዘጋጀት ተሠማርተዋል።

3,ATMO (የስልጠና ትምህርት)

ለልምምድ፣ ተሳታፊዎቹ፤ ከሳቴላይት የአቅጣጫ መጠቆሚያ ንዑስ መሣሪያ ተሰጥቶአቸው ያን በአጅ ይዘው፤ በዛ ላሉ ሰዓቶች፤ በጁባ በህንጻዎችና በጎዳናዎች ማዕዘን ያለውን ርቀትና ትክክለኛ አቀማመጥ ይለካሉ። በመጨረሻም በመለካት ያገኙአቸውን ውጤቶች በአጠቃላይ ኮምፑዩተር ውስጥ እንዲመዘገቡ ያደርጋሉ።

Archiv Ölfeld Bentiu zu Sudan Kämpfe
ምስል AP

ፕሮፌሰር Bernd Meissner በጀርመንና በ 4 የአፍሪቃ ሃገራት ዩንቨርስቲዎች፣የሳይንስ ፕሮጀክቶች አሏቸው።

4,«በሚመጡት 2 ዓመታት የጁባን የከተማ ካርታ አሰናድተን ለማቅረብ ነው የምንሻው።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ