1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳንና አከራካሪው የሞቱ ቅጣት

ቅዳሜ፣ ኅዳር 1 2005

ደቡብ ሱዳን የሞቱን ቅጣት ለተወሰነ ጊዜ እንድታቆም ብዙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰሞኑን ጥያቄ አቀረቡ። የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኒሀል ዴንግ ኒሀል የሞቱ ቅጣት ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም የተዘጋጀውን ሰነድ እንዲፈርሙ በመጠየቅ

https://p.dw.com/p/16gKP
Der Südsudan (arabisch ‏جنوب السودان‎ Dschanub as-Sudan, DMG Ǧanūb as-Sūdān, englisch Southern Sudan oder auch South Sudan) ist der südliche Teil des Sudan. Er war 1972–1983 und ist erneut seit 2005 eine autonome Region des Landes. Im Januar 2011 fand ein Referendum statt, in dem sich die Abstimmenden mit großer Mehrheit für die Unabhängigkeit entschieden.[1][2] Die Unabhängigkeitserklärung ist für den 9. Juli 2011 vorgesehen.[3][4] Als künftiger offizieller Landesname wurde Republic of South Sudan (RoSS) festgelegt.

ደብዳቤ የላኩት ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፡ ሂውማን ራይትስ ዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የደቡብ ሱዳን ድርጅቶች ለዚሁ ጥያቄአቸው መደገፊያ ይሆናል በሚል የሰጡት ምክንያት እአአ ሀምሌ 2011 ዓም ነፃ መንግሥት ያቋቋመችው ደቡብ ሱዳን የምትሠራበት የፍትሕ አውታር የሞት ፍርድ የተበየነባቸውን ግለሰቦች መሠረታዊ መብት አያከብርም የሚል ነው።
ደቡብ ሱዳን እስከዛሬ የሞቱን ቅጣት ተግባራዊ በማድረግ ላይ የምትገኘው በፍትሑ አውታርዋ ውስጥ በሚታዩት  ስህተቶች የተነሳ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይናገራል። አዲስቷ ሀገር ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ጊዜ የፖሊስ ኃይሏን እና የፍትሕ አውታርዋን እየገነባች ነው።  በፈረንሣይ ሀገር የሚገኘው የሂውመን ራይትስ ዎች አስተባባሪ ዦን ማሪ ፋርዶ እንዳስታወቁት፡ በዚሁ ስህተት የተነሳ በቅርቡ የሞቱ ቅጣት የሚጠብቃቸው እና ፅዳት በሌላቸው የወህኒ ቤት ክፍሎች ውስጥ በሠንሠለት ታስረው ቀናቸውን በመቁጠር ላይ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ቁጥር ጥቂት አይደለም።
« ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ ግለሰቦች ናቸው በጁባ እና በሌሎች የደቡብ ሱዳን ከተሞች እሥር ቤቶች የሞት ፍርድ ተበይኖባቸው ቅጣታቸው የሚፈፀምበትን ቀን በየወህኒ ቤቱ በመጠበቅ ላይ የሚገኙት። እነዚህ ሁለት መቶ ሰዎች ደግሞ ትክክለኛ ችሎት አላገኙም፤ ጠበቃ የላቸውም፤ በመሠረቱ የሞቱ ቅጣት ተቀባይነት የሌለው አሰራር ነው። እና የሞቱ ፍርድ ትክክለኛ ባልሆነ ችሎት የተበየነን የሞትን ቅጣት እኛን የመሰለ የመብት ተሟጋች ድርጅት በፍፁም ሊቀበለው አይችልም። »
ባለፈው ነሀሴ ወር መጨረሻ በጁባ ወህኒ ቤት በስቅላት የተገደሉት ሁለት እሥረኞች ፍፁም ትክክለኛ ችሎት ያላገኙበት ድርጊት በጣም አሳፋሪ ሆኖዋል። መብታቸውን ለማስከበር ዕድል ሳያገኙ ነበር የተገደሉት። በአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ መሠረት፡ ደቡብ ሱዳን ውስጥ እአአ በ 2011 ዓም ቢያንስ አምሥት ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል። የሞቱ ቅጣት ስለተፈፀመባቸው ግለሰቦች አሟሟት፡ ስለ ችሎታቸው እና ስለ ቅጣቱ አፈፃፀም በቂ መረጃ አለመኖሩን አሳሳቢ የሚሉት የመብት ተሟጋቾች ደቡብ ሱዳናውያን ስለሞቱ ቅጣት ተገቢውን ግምገማ ማካሄድ ይችሉ ዘንድ ግልፅነት ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።      
« በወቅቱ የሞቱ ቅጣት የሚፈፀምበት ዕቅድ ተይዞ ስለመሆን አለመሆኑ የምናውቀው ጉዳይ የለም። ግን ከሁለት መቶዎቹ የአንዳንዶች ቅጣት በዚህ ወር ወይም በቅርቡ እንደሚፈፀም እንገምታለን። ለዚህም ነው የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት የሞቱን ቅጣት ለተወሰነ ጊዜ እንዲያስቆሙ አሁን አስቸኳዩን ጥሪያችንን ያስተላለፍነው። እና የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት  እንዲሁም፡ ሌሎች 37 አፍሪቃውያት ሀገራት የሞቱ ቅጣት እንዲሻር የሚጠይቀውን ዓለም አቀፍ ሰነድ እንዲሚያፀድቁ ተስፋ እናደርጋለን።
የሞት ቅጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ መሠረታዊውን የሰብዓዊ መብት የሚጥስ፡ መሻር ያለበት አሰራር መሆኑን የመብት ተሟጋቾቹ ድርጅቶች በጋራ አሳስበዋል።
ለደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ይህንኑ ጥያቄ የያዘውን ደብዳቤ ያቀረቡት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፡ ሂውማን ራይትስ ዎች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ የደቡብ ሱዳን ድርጅቶች እስካሁን ለዚሁ ጥያቄአቸው መልስ አላገኙም። ግን ደቡብ ሱዳን የፊታችን ታህሳስ ወር የሞቱን ቅጣት እንዲሻር በሚጠይቀው የተመድ ሰነድ ላይ ድምፅ በምትሰጥበት ጊዜ ለጥያቄአቸው መልስ እንደሚያገኙ ብለን እናስባለን።» በዚሁ ጊዜ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሞቱን ቅጣት ለተወሰነ ጊዜ፡ በኋላም ባጠቃላይ ለመሻር ድፍረቱ ይኖራቸዋል ብለን ተስፋ አድርገናል። »
ከ137 የተመድ እና ከ 54 የአፍሪቃ ህብረት አባል ሀገራት መካከል ሁለት ሦስተኛው የሞቱን ቅጣት ሽረዋል፤ ቡሩንዲ፡ ኮት ዲ ቯር፡ ጋቦ፡ ርዋንዳ፡ ሴኔጋል እና ቶጎም የሞቱን ቅጣት የሻሩ ሀገራትን ቡድን ከጥቂት ጊዜ በፊት ተቀላቅለዋል። ደቡብ ሱዳንም ይህንኑ ቡድን ሳትዘገይ እንደምትቀላቀል የመብት ተሟጋቾቹ ድርጅቶች ተስፋቸውን ገልጸዋል።  

South Sudan's President Salva Kiir sits at the meeting table at the Sheraton hotel in Ethiopia's capital Addis Ababa September 25, 2012. Sudan and South Sudan leaders will try again on Tuesday to seal a border security deal after failing to achieve a breakthrough in the previous two days, officials said on Monday as both sides disagreed over whether progress had been made. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters
Ein nachgebauter Galgen steht am Freitag (19.02.2010) im Eingangsbereich des Neanderthal Museums in Mettmann. Er gehört zu der Sonderaustellung "Galgen, Rad und Scheiterhaufen", die bis zum 27. Juni 2010 Einblicke in den gruseligen Leistungskatalog der Strafen und seine Orte im 17. Jahrhundert gibt. Foto: Roland Weihrauch dpa/lnw (zu KORR:" Henker, Beil und Galgen - Museum zeigt das Grauen")
ምስል picture-alliance/dpa

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን