1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን ፤ አዲስ ውጊያና አዲስ መከራ

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2007

የደቡብ ሱዳን የእርስ- በርስ ውጊያ አንደገና በማገርሸት ፣ አገር -ምድሩን እንደ ሰደድ እሳት መለብለብ ጀምሯል። ቀየውን እየለቀቀ መሰደድ የጀመረው ሕዝብ ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን ይጠጋል። ሰላም ይበልጥ እየራቀ ሄዷል። የሰብአዊ ርዳታ ድርጅቶች

https://p.dw.com/p/1FTMi
ምስል Pawel Krzysiek

[No title]

ደግሞ፣ አስከፊ የረሃብ ዕልቂት እንዳይከሠት በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይ ፤ በነዳጅ ሃብት ክምችት በታወቀው የሀገሪቱ ሰሜናዊ አውራጃ፤ ውጊያው እጅግ መፋፋሙ ነው የሚነገረው።

አብዛኞቹ የርዳታ ድርጅቶች ፤ ከውጊው ቀጣና ለቀው ወጥተዋል። ግማሽ ሚሊዮን ያህል ሕዝብ፣ አሁን ርዳታ የተቋረጠበት መሆኑን፤ የተመሠቃቀለችው ሀገር የተባበሩት መንግሥታት ተጠሪ ቶቢ ላንትዘር በዚህ ሳምንት ውስጥ አስረድተዋል። የ ተ መ ድ በተጨማሪ እንዳለው ከ 12 ሚሊዮኑ ደቡብ ሱዳናውያን መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ያለምግብ ርዳታ ለዕልቂት ነው የሚዳረጉት።ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር ሠራተኞችም አሁን ክፉኛ የተጎዱትን ብቻ ነው በመንከባከብ ላይ የሚገኙት። በጁባ የ ICRC ሠራተኛ Pawel Krzysiek --

«ዓለም አቀፉን ቀይ መስቀል ማሕበር የሚያሳስበው ትልቅ ጉዳይ የሲቭሎች ዕጣ ፈንታ ነው። በዚህ ወቅት ፤ የዝናም ጊዜ በመሆኑ ፣ ሕዝቡ ፣ እህል የሚዘራበትና በመጪው የአዝመራ ጊዜ፣ የተሻለ እህል መሰብሰብ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር በቻለ ነበር።የምግብ ርዳታ ማከፋፈሉን ከራስ ምርት ጋር ማነጻጸር አይቻልም። ይሁንና ዘር የመዝራቱ፤ አትክልትም የመትከያው ሥራ ሁሉ ተጨናግፏል።»

Pawel Krzysiek እንዳብራሩት ከጦርነት ለመሸሽ ሲሉ ቤተሰቦች ፤ ትንንሽ ሕጻናትን ይዞ መጓዙ ተጨማሪ ፈተና ነው። አንዳንድ የልጆች በሽታዎች አሉ፤ የምግብ እጥረት አለ ። 250,000 ሕጻናት ናቸው የዚህ መሳደድ ሰለባዎች የሆኑት። ሌላም ተጨማሪ አሳሳቢ ሁኔታ አለ።

«በ Upper Nile ክፍለ ሀገር የምትገኘው የኮዶክ ሁኔታ እንቅልፍ ይነሳናልr። በዚያ የሚገኘው የእኛ ቡድን ፣ ከ 2 ቀናት በፊት በዚያ ውጊያ ማገርሸቱን ገልጿል። ይህም ICRC እና በዚያ ተክሎት የነበረው የጤና ተቋም ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር ማድግ እንደሚበጅ ተነግሯል። እጅግ አሳዛኝ ዜና ነው። በዚያ አካባቢ በየሳምንቱ 600 ያህል ሕሙማንን ተመላላሾችን ጭምር እንዲሁም ሕጻናትን ያክም የነበረው ይኸው የጤና ተቋም ነው።»

Flüchtlinge im Südsudan
ምስል AFP/Getty Images/C. Lomodong

በአማጽያኑ ላይ ብርቱ የማጥቃት ዘመቻ የከፈተው የደቡብ ሱዳን ጦር ሠራዊት፣ ሰላም ይወርድ ዘንድ ሲጥር እንደቆየ የሚነገርለት «ኢጋድ» እንደሚገምተው ከሆነ ፣ በሲቭሎች ላይ የኃይል ርምጃ ተወስዷል፤ መንደሮች ተደምስሰዋል። ይህ ደግሞ አንዳች ይቅርታ የማይደረግለት እኩይ ተግባር ነው። ጦር ሠራዊቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት UNITY በተባለው ፌደራል ክፍለ ሀገር የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ፤ ከዚያ ወዲህም በጆንግላይ እና UPPER NILE አስፋፍቷል። ዓለምአቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት HRW ታዲያ በዚህ ጊዜ ውስጥ በዘፈቀደ ሰዎች እየተያዙ መደብድብ፤ በግፍ ርምጃም ቁምስቅል ማየታቸው እንዳልቀረ ገልጿል። --በአቢጃ ፤ የድርጅቱ ቢሮ መግለጫ የሰጡት ሌስሊ ሌፍኮቭ --

«HRW የመዘገበው ብዙ ጉዳይ አለ፤ ጦር ሠራዊቱና ብሔራዊው የመረጃ ክፍል ይዘው ያሠሯቸው ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። እነርሱንም አልፎ-አልፎ በግፍ ርምጃ ቁም ስቅል ማሳየትና ስደተኞችን መደብደብ የተለመደ ሆኖ ዘልቋል። ይህ ዓይነቱ የግፍ ተግባር፣ የተፈጸመው በተፋላሚ ኃይሎች ቁርቁስ፣ የሕዝቡ አጠቃላይ ይዞታ አሳሳቢ እየሆነ በመጣበት ሂደት ነው። ይህ ዓይነቱ የአሥራትና ቁምስቅል መሳያ የግፍ ርምጃ ሲካሄድ የቆየበት ሁኔታ፤ ወይም ይህ የሰብአዊ መብት ክፉኛ መጣስ ለረጅም ጊዜ ሳይታወቅ ቆይቷል።»

ደቡብ ሱዳን ፣ እ ጎ አ ከሐምሌ ወር 2011 አንስቶ ነጻ ሀገር መሆኗ ቢታወቅም፤ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የቆየ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ቀድሞ ምክትላቸው በነበሩት ሪኤክ ማቻር መካከል የነበረ የረጅም ጊዜ የሥልጣን መቀናቀን በታኅሳስ 2006 ይፋ ወጥቶ ደም ወደሚያፋስስ ውዝግብ መለወጡ የታወቀ ነው።

Bildkombo Südsudan Riek Machar und Salva Kiir
ምስል Getty Images/Zacharias Abubeker/Ashraf Shazly/Montage

ሁለቱ ተቀናቃኞች፤ የጎሣዎቻቸውን አባላት ክተት ብለው ሕዝቡን ለሥቃይና መከራ ዳርገውታል። እስካለፈው የካቲት ወር ማለቂያ ገደማ ድረስ አዲስ አበባ ውስጥ በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ውይይቶች ሳይሠምሩ ነው የቀሩት።

«ከ 24 በማያንሱ ምንልባትም በሚበልጡ የሕጻናት ጉዳዮች ላይ ማረጋገጫዎችን ለማግኘት በቅተናል። ያም ሆኖ፤ ይህ ፣ በዛ ካለው ወይም ሥፍር ቁጥር ከሌለው ከፊሉ ነው። ስለችግሩ መጠነ- ሰፊነት በጣም አነስተኛ የሆነውን ሥዕል ማሳያም ሆነ ወካይ ነጥብ ነው።»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ