1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃዊቱ አትሌት የገጠማት ፈተና

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2011

በቅርቡ የዓለም አትሌትኪስ ፌደሬሽኖች ማኅበር IAAF በሰዉነታቸዉ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ testosterone የተባለ ንጥረ ነገር ያለባቸዉ አትሌቶች የንጥረ ነገሩን መጠን የሚቀንስ መድሐኒት እንዲወስዱ ያሳለፈዉን ሕግ በመቃወም ለዓለም የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት አቤት ብላ ነበር።

https://p.dw.com/p/3HtnI
Leichtathletik Sportlerin Caster Semenya
ምስል picture-alliance/dpa/H. Hanschke

የደቡብ አፍሪቃዊቱ አትሌት ጣጣ

የፆታ ምርመራና ዉዝግብ ያልተለያት ደቡብ አፍሪቃዊቱ አትሌት ካስተር ስሜንያ ሰሞኑን የሌላ ዉዝግብ ምክንያት ሆናለች።የ8መቶ ሜትር ሯጭዋ ስሜንያ ቀዚሕ ቀደም ሴትነትዋ ያጠራጥራል በሚል በተከታታይ ጥያቄና ምርመራ ሲደረግላት ነበር።በቅርቡ የዓለም አትሌትኪስ ፌደሬሽኖች ማሕበር IAAF በሰዉነታቸዉ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ testosterone የተባለ ንጥረ ነገር ያለባቸዉ አትሌቶች የንጥረ ነገሩን መጠን የሚቀንስ መድሐኒት እንዲወስዱ  ያሳለፈዉን ሕግ በመቃወም ለዓለም የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት አቤት ብላ ነበር።ፍርድ ቤቱ ግን አቤታተዉን ዉድቅ አድርጎ አትሌቷ የIAAF ደንብን እንድታከብር ወስኗል።

ኃይማኖት ጥሩነሕ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ