1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃዊዉ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ አረፉ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22 2012

ታዋቂዉ ደቡብ አፍሪቃዊ የፀረ-አፓርታይድ ታጋይ ዴኒስ ጎልድንበርግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ከቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር በጎርጎረሳዉያኑ 1966 ዓ.ም በደቡብ አፍሪቃዉ አፓርታይድ አገዛዝ ለፍርድ ቀርበዉ  22 ዓመት በጽኑ እስራት እስርቤት ማቀዋል።

https://p.dw.com/p/3bcvh
Südafrika Denis Goldberg Bürgerrechtler
ምስል picture-alliance/empics/N. Ansell

ታዋቂዉ ደቡብ አፍሪቃዊ ፀረ-ዘር አድልዎ ሥርዓት ታጋይ ዴኒስ ጎልድንበርግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።  የባህል እና የትምህርት ማዕከል የሆነዉ«ዴኒስ ጎልድንበር ሌጋሲ ፋዉንዴሽን ትረስት» በመባል በስማቸዉ የተከፈተዉ ድርጅት ዛሬ ይፋ እንዳደረገዉ ጎልድንበርግ ባደረባቸዉ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ነዉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።  87 ዓመታቸዉ ነበር። ከአይሁዳዉያን ቤተሰብ የሚወለዱት ታዋቂዉ የፀረ አፓርታይድ ታጋይ ዴኒስ ጎልድንበርግ የዘር መድሎ ሲያደርስ የነበረዉን የደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ መንግሥት በመታገላቸዉ የታወቁ ነጭ ደቡብ አፍሪቃዊ ነበሩ። የምህንድስና ባለሞያዉ ደቡብ አፍሪቃዊ ዴኒስ ጎልድንበርግ፣ ከቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ከኔልሰን ማንዴላ ጋር በጎርጎረሳዉያኑ 1966 ዓ.ም በደቡብ አፍሪቃዉ አፓርታይድ አገዛዝ ለፍርድ ቀርበዉ  22 ዓመት በጽኑ እስራት እስርቤት ማቀዋል። ጎልድንበርግ ከእስር ቤት እንደወጡ በስደት ብሪታንያ መዲና ለንደን ኖረዉ ወደ ትዉልድ ሃገራቸዉ ወደ ደቡብ አፍሪቃ የተመለሱት በጎርጎረሳዉያኑ 2002 ዓ.ም ነበር።     

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ