1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃ እና የአፓርታይድን ሥርዓት ያበቃው ሬፈረንደም

ሐሙስ፣ መጋቢት 6 1999

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ከአሥራ አምስት ዓመት በፊት፡

https://p.dw.com/p/E0bE

ልክ በዛሬዋ ቀን ነጮቹ የሀገሪቱ ዜጎች ብቻ የተሳተፉበት የመጨረሻው ምርጫ ተካሄደ። የዚያን ጊዜው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ፍሬድሪክ ቪሌም ደ ክለርክ የመሩት የሀገሪቱ መንግሥት የአፓርታይድን አገዛዝ ለመገርሠሥ የጀመረውን የተሐድሶ ለውጥ ነጮቹ ዜጎቹ መደገፍ አለመደገፋቸውን በሬፈረንደም እንዲወስኑ ምርጫ ማካሄዱ ይታወሳል። ድምፅ የመስጠት መብት ከነበራቸው ሁለት ሚልዮኑ ነጮች መካከል ስድሳ ዘጠኝ ከመቶው የውሁዳኑ አገዛዝ እንዲያበቃ ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ይኸው ውሳኔአቸውም እአአ በ 1994 ዓም ለተካሄደውና የሀገሪቱ ሥልጣን በብዙኃኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን እጅ እንዲያዝ ላደረገው የመጀመሪያው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንገድ ከፋች ሆኖዋል። ነጮች ደቡብ አፍሪቃውያን ከአንድ አሠርተ ዓመት ተኩል በፊት የሰጡትን ውሳኔአቸው ዛሬ እንዴት ይመለከቱታል።