1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያዉያን መከራ

ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2007

ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የታሰሩ 55 ኢትዮጵያዉን ገንዘብ ካልከፈላችሁ ከእስር ቤት አትወጡም ተብለዉ መያዛቸዉ ተሰማ። ይህን የገለፁልን ለዶይቼ ቬለ በእጅ ስልክ የፅሁፍ መልዕክት የላኩልን እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ከተያዙት መካከል ገንዘብ ከፍለዉ የተወሰኑት መለቀቃቸዉን ገልጸዉልናል።

https://p.dw.com/p/1FilX
Infografik Geplante Stromtrassen für kongolesisches Inga-Staudammprojekt Portugiesisch

የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስለጉዳዩ የሰማዉ እንደሌለ ነዉ ለዶይቼ ቬለ የገለፀዉ። ወደደቡብ አፍሪቃ ለመግባት የሚሞክሩ ኢትዮጵያዉያን ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ማኅረሰብ ሊቀመንበር አቶ ታምሩ አበበ እንደሚሉት በተደጋጋሚ ድንበር ለማለፍ ሲሞክሩ በሀገሪቱ መንግስት ኃይሎች መያዝ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዉያንም እየታገታሉ። እሳቸዉ እንደሚሉት ደቡብ አፍሪቃ የሚገቡና የገቡ ኢትዮጵያዉያን እዚያዉ ያለዉ የሀገሬዉ የዘር ጥላቻ ጥቃት ሳያንሳቸዉ በራሳቸዉ በኢትዮጵያን ሕገ ወጥ ከሀገር ሀገር ሰዉ አሸጋጋሪዎች እየታገሩ ገንዘብ ዉለዱ ይባላሉ።

Flüchtlingslager, Immigranten suchen Schutz vor fremdenfeindlicher Gewalt in Johannesburg, Südafrika
የስደተኞች መጠለያ በደቡብ አፍሪቃምስል picture-alliance/ dpa

እንደአቶ ታምሩ ገለፃ ከሆነ በአሁኑ ወቅት ወደደቡብ አፍሪቃ የሚገቡት አብዛኞቹ ከደቡብ ኢትዮጵያ ቤት ንብረትና ከብቶች እየሸጡ የቋጠሯትን ለሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች በመገበር ከአፍሪቃዋ የበለፀገ ኤኮኖሚ ባለቤት የማንዴላ ሀገር ገንዘብ ለመዛቅ የተመኙ የዋሆች ናቸዉ። በዛሬዉ ዕለት እንኳን ከእስርመፈታታቸዉየተነገራቸዉ30 ሰዎች በሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ ማላዊ ድረስ ተሸኝተዉ የድንበር አጥር በጥሰዉ ሲገቡ በመንግሥት ጠባቂዎች እጅ የገቡ ነበሩ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ቤት የጀመረዉ ሕገወጥ አሸጋጋሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ርምጃ ወደሌሎች አካባቢዎችም ሰንሰለቱን ተከትሎ ቢቀጥል የብዙዎችን ሕይወት ከአደጋ ለማዳን እንደሚችልም አቶ ታምሩ አመልክተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ