1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር፤ የSABC ደንብ ከሳንሱር የሚቆጠር ነዉ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2008

የድርጅቱ ባለሥልጣናትን ደንቡን አናከብርም ያሉ ስምንት ጋዜጠኞችን አባርረዋል ወይም ከሥራ አግደዋል።ጋዜጠኞቹ በበኩላቸዉ አዲሱ ደንብ በሐገሪቱን የተደረገገዉን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የመዘገብ ነፃነትን የሚፃረር ነዉ ባዮች ናቸዉ

https://p.dw.com/p/1JTEG
ደቡብ አፍሪቃ፤ የጋዘጠኞች መብት
ምስል Julie Reid

[No title]

የደቡብ አፈሪቃ ማሰራጪያ ድርጅት (SABC) የተሰኘዉ የሐገሪቱ ትልቅ መገናኛ ዘዴ አዲስ ያወጣዉ ደንብ የድርጅቱን ሐላፊዎች ከጋዜጠኞች ጋር እያጋጨ ነዉ።የድርጅቱ ባለሥልጣናት ደንቡን አናከብርም ያሉ ስምንት ጋዜጠኞችን አባርረዋል ወይም ከሥራ አግደዋል።ጋዜጠኞቹ በበኩላቸዉ አዲሱ ደንብ በሐገሪቱ የተደረገገዉን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የመዘገብ ነፃነትን የሚፃረር ነዉ ባዮች ናቸዉ።የተለያዩ ማሕበራትና የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም ለጋዜጠኞቹ ድጋፋቸዉን እየገለጡ ነዉ። የደቡብ አፍሪቃ ተባባሪ ዘጋቢያችንን አነጋግረነዋል።

መላኩ አያሌዉ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ