1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደን ሕይወት ነዉ

እሑድ፣ ሚያዝያ 19 2006

በአካባቢያቸዉ የሚገኝና ለእነሱ የዕለት ተዕለት ህይወት ትርጉም ያለዉ የደን ሃብት የምንጠራ አደጋ ባንዣበበበት ወቅት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የመዠንገር ማኅበረሰብ አባላት «መዠንገሮች ዉሃ ብቻ ሳይሆን ደግም ህይወት ነዉ» የሚል መመሪያ እንዳላቸዉ ገልጸዉልን ነበር።

https://p.dw.com/p/1Boht
Äthiopien Omo Fluss Tal Landschaft
ምስል JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages

ደን ሕወት ነዉ የሚባለዉም ያለምክንያት አይደለም። በሚገኝበት ስፍራ ለአካባቢ ተፈጥሮዉ፤ ለአየር ጠባዩ ሚዛን፣ ለአካባቢዉ ማኅበረሰብ ና ዕለታዊ ኑሮም ሆነ በሀገርም ደረጃ የሚሰጠዉ ኤኮኖሚያዊ ጥቅም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በአንድ ወቅት እጅግ መመናመኑ የዘርፉን ምሁራን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ሲያሳብ እና ሲያነጋግር ቆይቷል ዛሬም እያነጋገረ ነዉ። በአንፃሩ ደንን ለማልማት በመንግስታዊ መሥሪያ ቤቶችም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሳይቀር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመረዉ ጥረት አበረታች ነዉ። ዶቼ ቬለ በኢትዮጵያ የደን ይዞታና ደንን ለማበልጸግ የሚደረጉ ሥራዎች ላይ ዉይይት አካሂዷል።

ሙሉዉን ዉይይት ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ