1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዲሽታ-ጊና፤ የታሪኩ ጋንኪስ የእንዋደድ  ዜማ

እሑድ፣ ሚያዝያ 10 2013

«ዲሽታ ጊና» በአሪ ብሄረሰብ ዘንድ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን፤ በዓሉ የመረዳዳት፣ የአንድነትና  የዕርቅ በዓልም ጭምር ነው።ድምፃዊ ታሪኩ ጋነኪስ ይህንን ሙዚቃ የሰራው አንድም የብሄረሰቡን ባህል ለማስተዋወቅ በሌላ በኩል ደግሞ  ፍቅር፣ ሰላምና መተሳሰብ በኢትዮጵያውያን መካከል እንዲሰፍን ካለው ምኞት መሆኑን ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3s8uh
Musiker Tariku Gankise
ምስል Privat

ዲሽታ -ጊነ ፤ የታሪኩ ጋንኪስ አዲስ  ዜማ

ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሳ  በደቡብ  ክልል  ደቡብ ኦሞ ዞን ከሚገኙ 16 ብሄረሰቦች መካከል  አንዱ በሆነው በአሪ ብሄረሰብ ቋንቋ «ዲሽታ ጊና» በሚል በቅርቡ አዲስ ተወዳጅ ዜማ ለአድማጭ ጀሮ አድርሷል ። «ዲሽታ ጊና» በአሪ ብሄረሰብ ዘንድ  በጥር ወር የሚከበር የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን፤ በዓሉ የመረዳዳት፣ የአንድነትና  የዕርቅ በዓልም ጭምር ነው።ድምፃዊው  ይህንን በዓል በተመለከተ ሙዚቃ መስራት የፈለገውም አንድም የብሄረሰቡን ባህል ለማስተዋወቅ በሌላ በኩል ደግሞ  ፍቅር፣ ሰላምና መተሳሰብ በኢትዮትዮጵያውያን መካከል እንዲሰፍን ካለው ምኞት መሆኑን ይገልጻል።
ድምፃዊ ታሪኩ ጋንኪሳ ተወልዶ ባደገባት ጅንካ፤ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኦሞ የባህል ቡድን ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ የተለያዩ ባህላዊ ዜማዎችን  በመጫወት ላይ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደምምም «ውቧ ጅንካ» የሚል ነጠላ ዜማ ለአድማጭ ጀሮ አብቅቷል።
 በሙዚቃው ከአድማጩ ያገኘው ምላሽ «ህዝቡ ምን ያህል  ፍቅርና ሰላም እንደናፈቀው።» የሚያሳይ ነው የሚለው ታሪኩ፤  በሀገሪቱ ዕርቅ፣ፍቅር፣ አንድነትና ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርጉ ሙዚቃዎችና ሌሎች የኪነ-ጥበብ ሥራዎች እንዲሰሩ በማገዝ መንግስት የበኩሉን ቢወጣ መልካም መሆኑን ገልጿል።  

Äthiopien | Musiker Tariku Gankise
ምስል Privat

 ሙሉ ዝገጀቱን የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ፀሀይ ጫኔ

ማነተጋፍቶት ስለሺ