ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ በአሜሪካ

አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
12:19 ደቂቃ
08.07.2018

ዲዛይነር ተሻለች ታደሰ በአሜሪካ

በዳላስ ቴክሳሱ የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን ፎቶግራፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በሸማ ላይ አትማ አቅርባለች። «እግዚአብሔር የሰጠን መሪ» ያለቻቸውን ዶክተር ዐብይን «ስለምወዳቸው ነው የሰራሁት» ትላለች። «የኤኮኖሚ ዋልታ» ሆነውኛልም ብላለች ተሻለች።

ኢትዮጵያ ውስጥ የእንሰት ውጤቶችን ከሸማ እና ከጥለት ጋር በመቀላቀል በምታመርታቸው ባህላዊ ልብሶች ጫማዎች ቦርሳዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ትታወቃለች።

ከጉራጌ ቤተሰብ የወጣችው ይህች የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ባለቤት አዶት ዲዛይን በተባለው ድርጅቷ በምታቀርባቸው የተለያዩ የፋሽን ትርዒቶችም እንዲሁ እውቅና አትርፋለች። ከሁለት ዓመት ወዲህ በምትኖርበት በአሜሪካንምሥራዎችዋን ማምረት እና  ማስተዋወቅዋን ቀጥላለች። ዲዛይነር ወይም የእጅ ሥራ ባለሞያ ተሻለች ታደሰ።  በዳላስ ቴክሳሱ የሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያውያን ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን ፎቶግራፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በሸማ ላይ አትማ አቅርባለች። «እግዚአብሔር የሰጠን መሪ» ያለቻቸውን ዶክተር ዐብይን «ስለምወዳቸው ነው የሰራሁት» ትላለች። «የኤኮኖሚ ዋልታ» ሆነውኛልም ብላለች ተሻለች።ሙያዋን ለማሻሻል በምትኖርበት በሂዩስተን የፋሽን ዲዛይን አካዳሚ ውስጥ እየተማረች ምርቶችዋንም እያስተዋወቀች መሆኑን ተናግራለች። የፈጠራ ዲዛይን እለታዊ ሕይወቴን የምገልጽበት ነው የምትለው ተሻለች ዲዛይን ለኔ የአሁንን ማየት ነውም ትላለች። የመጀመሪያ እርካታዋ ዐዕምሮዋ ላይ ያለውን ሀሳብ በስራ ስትተረጉም ነው። ሁለተኛው ደግሞ ሰዎች ሥራዋን አይተው ሲወዱት ከዚያም ሰው ሲጠቀምበት በመጨረሻም አብረዋት የሚሰሩ ውጤታማ ሲሆኑ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም ትላለች። ምርቶቿን ከምትሸጥበት እና ከምታስተዋውቅበት ስፍራ ላይ ሆኖ በስልክ አነጋግሬያታለሁ። ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ

ኂሩት መለሰ 

አዜብ ታደሰ