1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድህነት እና ረሀብ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 5 1996

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ መርሐ ግብር መሥሪያ ቤት የረሀብ አደጋ በዓለም በመስፋፋት ላይ መሆኑን አስጠነቀቀ። መሥሪያ ቤቱ ዛሬ በመላ ዓለም ታስቦ የዋለውን የዓለም ምግብ ቀን ምክንያት በማድረግ ከዠኔቭ እንዳስረዳው፡ በአርባ ዓመት ታሪኩ ውስጥ እንዲህ እንደ አሁኑ ብዙ የምግብ ርዳታ አስፈልጎት አያውቅም። ረሀብና ያልተመጣጣነ አመጋገብ በዚህ በያዝነው ምዕተ ዓመትም በዓለም ዋነኞቹ የሞት ምክንያቶች የሆኑበትን ገሀድ መቀበሉ እጅግ እንደ

https://p.dw.com/p/E0gE

��ከብድ የመሥሪያ ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ ጄምስ ቲ ሞሪስ አስታውቀዋል። ይህንኑ ችግር በማስወገዱ ረገድ፡ ሞሪስ እንደሚሉት፡ መንግሥታት፡ የኤኮኖሚው ዘርፍ እና የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች በረሀብ አንፃር በሚደረገው ዘመቻ ላይ ጉልሁን ርብርብ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።


በሰው ልጅ ታሪክ እንዲህ እንዳሁኑ ምግብና ቁሣቁስ ተትረፍርፎ፡ በሌላ በኩል ደግሞ ድህነት፡ ያልተመጣጣነ አመጋገብና ረሀብ፡ እንዲሁም፡ ድህነትና ብልፅግና ተስፋፍቶ የሚያውቅበት ጊዜ አልነበረም። ይህ አሁን ባለው የዓለም ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ መፍትሔ ሊገኝለት የማይችል ተፃራሪ ገሀድ ነው። እንዲያውም ችግሩ ጭራሹን የእንደሚባባስ ነው የሚገለፀው። ምንም እንኳን የዚህኑ ችግር መንሥዔ የማወቁ ችሎታ ቢሻሻልም፡ በእጦትና በድሎት፡ በድህነትና በብልፅግና መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው የሄደውለየጊዜው በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጉባዔዎች ወይም ሣይንሣዊ ሴሚናሮች ላይ ይኸው ልዩነት ከመጉላቱ ጎን፡ አንዱ ወገን ዓለም በኤኮኖሚው እየተቀራረበች የተገኘችበትን ድርጊት እንደ ብልፅግና ሞተር ሲያሞግስ፡ ሌላው ወገን ግን ይኸው ሂደት ሀብታሙን ሀብታም፡ ድሀውን ድሀ የሚያደርግ ነው በሚል ወቀሳ ያሰማል።ምድራችን በበለፀገውና በድሀው ዓለም በሰሜንና በደቡብ፡ እንዲሁም፡ በኢንዱስትሪ፡ በአዳጊ እና በኢንዱስትሪ ጎዳና በማኮብኮብ ላይ ባሉ ሀገሮጭ ተከፋፍላለች። ይሁን እንጂ፡ ይህ አባባል፡ የወቅቱን ገሀድ ሁኔታ አያንፀባርቅም። እርግጥ፡ ድሆቹ፡ ያልተመጣጠነ አመጋገብ እና ረሀብ የሚያጠቃቸው ወገኖች በብዛት የሚገኙት በመልማት ላይ ባሉት ሀገሮች ውስጥ ነው። በዚሁ አካባቢ ስምንት መቶ ሚልዮን ሕዝብ ይራባል፤ አንድ ነጥብ ሁለት ሚልያርድ ደግሞ ከአንድ ዶላር ባነሠ ገንዘብ ሕይወቱን እንዲመራ ተገዶዋል። በሀብታሙ ሰሜንም ግን ቢሆን ቀደም ሲል የተጠቀሱት ችግሮች እየጨመሩ መጥተዋል። ወደ አርባ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ በእጦት በረሀብ እና ባልተመጣጠነ አመጋገብ እንደሚሠቃይ ቢገመትም፡ የበለፀገው ዓለም ጉዳዩን ተገቢ ትኩረት አልሰጠውም። ከዚህ ሌላ ደግሞ ፖለቲካው በአዳጊዎቹ ሀገሮች ውስጥ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የዕድገት እና የብልፅግና ደሴቶች ተፋጥነው ብቅ ማለት የያዙበትን ድርጊት ችላ ብሎታል። እሥያ ውስጥ በርካታ ሀገሮች፡ በተለይ ቻይና እንዲሁም አንዳንድ የላቲን አሜሪካ ሀገሮች ዓለም በኤኮኖሚው እየተቀራረበች የተገኘችበት ሂደት ግዙፍ ተጠቃሚ ሆነዋል። ይሁንና፡ ይኸው አዎንታዊ ሂደት በጠረፍ ባሉ አካባቢዎች ብቻ ተጠናክሮ ነው የሚታየው። እነዚህ በብልፅግናው ጎዳና ላይ የሚገኙት አካባቢዎች አዘውትረው በድህነት ካሉት ከራሳቸው መሀል ሀር ይልቅ ከኢንዱስትሪው ዓለም ጋር የበለጠ ግንኙነት አላቸው። ይህም በድሀውና ሀብታሙ መካከል ያለውን ልዩነት አስፍቶ ባካባቢው ውጥረት የሚካረርበት አሳሳቢ ሁኔታ እየፈጠረ ነው የተገኘው። ድህነትና ረሀብ ባንድ በኩል፡ ብልፅግናና ትርፍርፍ ምርት በሌላ ሂደት ያሳየው አንድ ጉዳይ ቢኖር ነፃው የዓለም ንግድ አሠራር ድሆቹ አዳጊ ሀገሮች ካሉበት የሥቃይ ማጥ ውስጥ መውጣት የሚችሉበትን ዕድል እንደማይሰጥ ነው። ምክንያቱም የበለፀጉት መንግሥታት የግብርና ምርታቸውን ለማሳደግ እያሉ ሦስት መቶ ሀምሳ ሚልያርድ ዶላር ድጎማ እስከሰጡና የዓለም ገበያዎችንም በርካሹ ምርታቸው እስካጥለቀለቁ ድረስ፡ ድሆቹ ሀገሮች ከዓለሙ ገበያ ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም። ይህ በመሆኑም ልዩነቱ መጥበብ ይኖሮበታል። ለዚህም በደቡባዊ ንፍቀ ክብብ የሚገኙት ድሆች ሀገሮች ሥር ነቀል መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግና ኃይላቸውን ባካባቢ ፕሮዤዎች ውስጥ እንዲያነቃቁ፡ ሰሜኑ ንፍቀ ክብበ ደግሞ በገበያዎቹ ላይ ያሳረፈውን የንግድ ማከላከያ ርምጃ እንዲያነሣ እና በትርፍርፍ ምርት ፍጆታ ላይ ያተኮረውን ልምዱን እንዲቀይር ሀሳብ ቀርቦዋል።