1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድምጻዊ ማሚላ በህክምና ላይ ይገኛል

እሑድ፣ ሚያዝያ 13 2011

ድምጻዊ እና የግጥም ደራሲ የሆነው ማሚላ ሉቃስ የሙዚቃ ቪዲዮውን በማዘጋጀት ላይ እንዳለ ጉዳት ደርሶበታል። በአሁኑ ሰዓት በህክምና ላይ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3H6Lo
Symbolbild Retro Notenblätter
ምስል Colourbox

ድምጻዊ የግጥምና የዜማ ደራሲ ማሚላ ሉቃስ

ድምጻዊ የግጥምና የዜማም ደራሲ ነው፤ ማሚላ ሉቃስ። ማሚላ «ኣቲ መለይ» የተሰኘውን አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ ለመሥራት ወደ አሰላ ተጉዞ ነበር፤ የዛሬ አንድ ወር ከአስር ቀን ገደማ። ማሚላ ለዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ (ክሊፕ) ቀረጻ  ላይ እያለ አደጋ ደርሶበታል። በአሁኑ ሰዓት ወላይታ በሚገኘው ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ነው። «ኣቲ መለይ» የተሰኘው የማሚላ የሙዚቃ ክሊፕ በቀጣይ ሳምንት እንደሚወጣ አጫውቶናል። ማሚላ ጋር ያደረግነውን ቆይታ ሙሉው ዝግጅት ማገናኛው ላይ ይገኛል

ነጃት ኢብራሂም

ማንተጋፍቶት ስለሺ